Get Mystery Box with random crypto!

አጠቃላይ በነበረው ሂደት 142 ክስ የተመሰረተባቸው ሰዎች ላይ የፌዴራል አቃቤ ህግ በፌደራል ከፍተ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

አጠቃላይ በነበረው ሂደት 142 ክስ የተመሰረተባቸው ሰዎች ላይ የፌዴራል አቃቤ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርባ ምንጭና አካባቢው በሚያስችለው ችሎት ላይ ክስ መስርቷል፤ ተጠርጣሪዎቹ ካሉበት ቦታ ወደዚያ ተዛውረው ክሳቸውን የሚከታተሉ ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ አካባቢ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ 247 ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያለው ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ሚያዚያ 18 /2014 ዓ.ም በተፈጥሮ ሞት የሞቱትን ታላቅ የእምነት አባት ሸክ ከማል ለጋስ የቀብር ስርዓታቸውን ለመፈጸም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 8 አካባቢ በሚገኘው ወደ ሀጅ ኤልያስ መካነ መቃብር የእስልምና እምነት ተከታዮች መካነ መቃብር ወደ ሆነው አስከሬናቸውን ለማኖር ወዳጅ ዘመዶቻቸው ወደ ቦታው በሄዱበት ከቀኑ 7ሰዓት30 ላይ በተለምዶ ቀሀ ወንዝ ከሚባለው ድንጋይ በማውጣ መቃብሩን ለማመቻቸት በሚደረግ ሂደት ውስጥ አስቀድሞ በአጎራባችነት የነበረ የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያመልኩበት አበራ ጊዮርጊስ የሚባል ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ የአብነት ተማሪዎች ከዚያ በፊት የድንበር ችግር በመኖሩ ድንጋዩን የሚወስዱት ድንበር ሊያካልሉ ነው በሚል ድንጋይ መወራወር ይጀምራሉ፤ በዚህ ሂደት አንደኛ ተከሳሽ የሆነው የቤተክርስቲያኑ ጥበቃ ጥይት ወደ ህዝቡ በመተኮስ ቦንብ እንዲወረወር በማድረጉ ምክንያት በዚያን ቅጽበት ብቻ ሶስት ሰዎች ሂይወታቸው አልፋል ብለዋል፡፡
ግጭቱ ተስፋፍቶ ወደ ከተማው በመሰራጨቱ በተከታታይ ቀናት የተለያዩ ግጭቶች መኖራቸውን የምርመራ መዝገባችን ያስረዳል ያሉት አቶ ፍቃዱ መጀመሪያ የጸጥታ ሀይሉ 509 ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ 310 ወንጀል ውስጥ መሳተፋቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ባለመገኘቱ ወዲያው እንደተለቀቁ ተናግረዋል፡፡

199 ቀድመው የተያዙና 17 ከዚያ በኋላ የተያዙ ሰዎችን አንድ ላይ በማድረግ በ216 ሰዎች ላይ የጊዜ ቀጠሮ እየተጠየቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ 121ቹ ወንጀል ስለመፈጸማቸው ማስረጃ ባለመኖሩ እንዲለቀቁ ተደርጎ በአጠቃላይ 77 የተያዙ፣ 62 ያልተያዙ ሰዎች ላይ ምርመራ ሲጣራ ቆይቷል፡፡ መጨረሻ 250 የሰው ምስክሮች ከተሰበሰበቡ በኋላ በፍርድ ቤት ክስ ሊያስመሰርትባቸው በሚችል 103 ሰዎች ከሁለቱም ዕምነቶች ተለይተው ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ 69 ተይዘው የታሰሩ 34 ደግሞ ተፈላጊዎች ሲሆኑ 24 የዕስልምና እምነት ተከታዮች፤ 79 ደግሞ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ናቸው፤ ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ሴቶች መሆናቸውን አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡

ግጭቱ ባህሪው ቀድሞ ታስቦበት ያልነበረ በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተፈጠረ ነገር ግን የሰፋ፤ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን የማምለኪያ ቦታ እና የንግድ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶችን በመምረጥ ጉዳት በማድረስ፤ የእስልምና ዕምነት ተከታዮችም ደግሞ አጸፋው የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች የንግድ ቦታ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የምርመራ ግኝታችን ያመለካክታልም ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው፡፡
አያይዘውም 20 ሰዎች ከሁለቱም ዕምነት በግጭቱ ለሞት ተዳርገዋል፣ ከ100 ሰዎች በላይ የአካል ጉዳት ደርሷል፣ 60 ሚሊዮን ግምት ያለው ንብረት ውድሟል፤ የዕስልምና ዕምነት ተከታች በዕምነቱ በኩል ያቋቋሟቸው ኮሚቴዎች ደግሞ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደርሷል ብሎ ያመጣ ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ በኩል ግን 60 ሚሊዮን የሚል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በስልጤ ዞን ከተፈጸመው ወንጀል ጋር በተያያዘ ወራቤ ሳንቁራ ወረዳ በአለም ገበያ ከተማና መንዝር ጦር በርበሬ ወረዳ በተባሉ አካባቢዎች የተፈጸመ ወንጀል በሚያዝያ 18 2ዐ14 ዓ.ም. ጎንደር የተከሰተውን ወንጀል ተከትሎ ማታ 2፡00 ሰዓት ከሰላት በኋላ አንድ አሰጋጅ እና አንድ ኡስታዝ ጎንደር የፈሰሰው ደም የናንተ ደም ነው፤ ጎንደር ሙስሊሙን የገደለው ክርስቲያን ነው ስለዚህ እንዲኖሩ መፍቀድ የለብንም ብለው የቀሰቀሱ በመሆኑ በማግስቱም ከቀኑ7፡00 ሰዓት ላይ በነበረው ሰላት ተመሳሳይ ቅስቀሳ በማድረጋቸው በትምህርት ቤቶችም በመቀስቀስ መስጊድ ተቃጥሏል ብሎ በማስወራት ወደ ብጥብጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

በወራቤ ከተማ ቅዱስ ሩፋኤል በተባለ ቤተክርስቲያን ላይ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ በመሄድ ቤንዚል እና የተለያዩ ስለታማ ነገሮችን በመያዝ ውድመት መጀመራቸውን የወራቤ ዩኒቭርስቲ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያናችን ተቃጠለ ብለው በመምጣታቸው ብጥብጡ መባባሱን በአካባቢው ባለው መስጊድም ሊቃጠል ነው የሚል የአዛን ድምጽ በማሰማት የሰው ቁጥር እንዲመጣ ተደርጎ ቤተክርስቲያኑ መቃጠሉን የምርመራ መዝገቡ ያሳያል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት ሌሎች ወረዳዎችም ጭምር 4 የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅዱሳትን ጨምሮ እንዲሁም 3 የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያናት መቃጠላቸውን እንዲሁም የዋጋ ግምቱ ወደ 46 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት መውደሙን የምርመራ ግኝቱ ያመላክታል፡፡
ሚኒስትር ዴዔታው እንደገለጹት ከሆነም የምርመራ መዛግብቱን መሰረት በማድረግ በ97 ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስቴር ዴኤታው በሁሉም ግጭት በተፈጸመባቸው ቦታዎች ውስጥ የጸጥታ መዋቀሩ ገብቶ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አንስተው፤ በቅርቡ በወለጋ ግንቢ አካባቢ የተፈጸመው ወንጀልን ጨምሮ መቻሬን እና ጋንቤላ የተፈጸመው ወንጀል ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ተናግረው፤ ወንጀል ሀይማኖትንና ብሄርን የማይወክል መሆኑን በመገንዘብ በየደረጃ ያለው የመንግስት አደረጃጀትና ህብረተሰብ ትብብር ሊያደርግ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0uvYmij9VMGPpdDDjuhqWtQCm6xmgLAYLggG2yzQRu7vFpkYCze9YvEFH37mipFZUl&id=100068870753847