Get Mystery Box with random crypto!

ሐምሌ 1 /2014 ዓ.ም ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሀ በዓልን አቅመ ደካሞችን በመርዳት እንዲያ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ሐምሌ 1 /2014 ዓ.ም

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሀ በዓልን አቅመ ደካሞችን በመርዳት እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ጥሪ አቀረቡ

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ሀጂ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ጥሪ አቀረቡ።

ሀጂ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ 1 ሺህ 443ኛውን የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ነገ በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ታላቁን የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም ወጥቶ አክብሮ በሰላም እንዲመለስ ጠይቀዋል፡፡

ሀጂ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ለኢዜአ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ሰላም የሁሉም መሰረት በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ታላቁ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በፍቅር፣በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡

ሀገር፣ ቤተሰብ፣ልማትና እድገት የሚኖረው ሰላም ሲኖር በመሆኑ ለሰላም ከፍ ያለ ዋጋ በመስጠት በሰዎች መካከል የትብብርና ወንድማማችነት መንፈስ ማስፈን ይገባልም ነው ያሉት።

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁን የአረፋ በዓል ሲያከብር አቅመ ደካሞችን በመጠየቅ፣ የተራቡትን በማብላት፣ የታረዙትን በማልበስ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ሀይማኖት የሚኖረው ሀገር ሲኖር መሆኑን በመረዳት በዓሉን ስናከብር በመተዛዘን፣ በመረዳዳትና አንድነትን በማጠናከር መሆን አለበትም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የሀይማኖት አባቶቹ 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል የሰላም፣ የደስታ፣ የብልጽግናና የመከባበር ይሆን ዘንድ የትብብር መንፈስ መጎልበት አለበት ብለዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100068870753847
Telegram:- https://t.me/gummerw
Youtub: -https://youtube.com/channel/UCyqat__kk7lXxzpRv8r7chA