Get Mystery Box with random crypto!

እነጀዋርን መግለጫው ለምን ቆጠቆጣቸው?? ••••••••••••• (ጉዳያችን) •••••••••••••• | Gudayachn ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚንኬሽን እና ምክር አገልግሎት Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

እነጀዋርን መግለጫው ለምን ቆጠቆጣቸው??
•••••••••••••
(ጉዳያችን)
••••••••••••••
ጀዋር መሐመድ፣በቀለ ገርባና ኦኤምኤን ባለፈው የአማራ ክልል እና የኦሮምያ ክልል መሪዎች ሸኔን ለመዋጋት በጋራ ያወጡትን መግለጫ እየኮነኑ ነው::ለመሆኑ መግለጫው ምን ስህተት ኖሮት ነው ይህንን ያህል የቆጠቆጣቸው?

ይህ ብቻ አይደለም፣ሦስቱም ዶ/ር መራራን ጨምሮ በሸኔ ላይ የሚደረገውን ዘመቻ በኦሮምያ ላይ የተዘመተ አስመስለው ሲናገሩ ተሰምተዋል::የሁለቱ ክልሎች መሪዎች ባለፈው በጋራ የሰጡትን መግለጫ "ሁለቱም ኦኤምኤንን ጨምሮ " የአማራና ኦሮምያ ክልሎች በጋራ ኦሮምያ ላይ ለመዝመት ጦርነት ያወጁበት" በማለት እያጥላሉ ገልፀውታል::

የአማራና የኦሮሞ ክልል ከተስማሙ የአማራ ልዩ ኃይል ቤኒሻንጉል እንደዘመተው ጊምቢ የማይዘምትበት ምን ምክንያት አለ?

ጀዋር ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ የአማራ ልዩ ኃይል ከሌላ አገር የመጣ ጦር ይመስል የሁለቱን ክልሎች መተባበር ናላውን አዙሮት፣ቀልቡን አሳጥቶት ሲናገር ታይቷል::

ጀዋር እና በቀለ ተረጋጉ! የክልሎች መተባበር እንዲህ የሚያሳብዳችሁ የኦሮምያ ችግር በሸኔ መደምሰስ ከተፈታ አጀንዳ ስለማይኖራችሁ ከአገር አገር እየዞሩ የምትበሉበት መተዳደርያ የእንጀራ ገመዳችሁ ሊበጠስባችሁ ስለሆነ ያስጮኻችኋል እንጂ የህዝብ መተባበር ምንም ጥፋት ሆኖ አይደለም::እንዲያውም መጥፎ ነገርን ወደ መልካም መቀየር ከተባለ የሸኔ የእልቂት አጀንዳ የአማራና ኦሮምያ በጋራ ወለጋ ዘምተው አገር ማረጋጋታቸው መሆን አለበት::

በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በወለጋ እየረገፉ ስለ ገዳዩ ሸኔ ሳታወሩ የአማራና ኦሮምያ ክልል በጥምረት ሸኔ ላይ እንዘምታለን ማለታቸው ቆጠቆጣችሁ::

የኦሮምያ ልዩ ኃይል ህወሓትን ለመዋጋት ወሎ እንደተገኘ ሁሉ፣ ክልሎቹ እስከተስማሙ ድረስ የአማራ ልዩ ኃይልም ጊምቢ ይገባል::ይህ ምንም የሕግ ጥሰት የለውም::

የሸኔ ዓላማ ሁለቱን ክልሎች ማባላት ነበር::የሁለቱ መተባበር ያቃጠላቸው እነጀዋር ቢያንስ ትብብሩን በመቃወም በቅናት በመቃጠል ሸኔን በልጠውታል ብቻ ሳይሆን ከሸኔ ጋር "ስልቻ ቀልቀሎ፣ቀልቀሎ ስልቻ" ሆነዋል::የመቶዎች በቀን መጨፍጨፍ ሳያሳዝናቸው የህዝብ መተባበር የሚያቃጥላቸው አሳፋሪዎች!