2022-07-07 21:45:50
አልገባችሁም!!!
•••••••••••••••
ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴን ፎቷቸውን እየዘቀዘቁ በ1966 በቮልስ ቮገን መኪና እንደ ተራ ሰው ሲወስዷቸው በሺህ የሚቆጠር ህዝብ ንጉሱን ሲሳደብ እርግጠኛ ሆኖ ነበር::ሀዲስ ዓለሜየሁ እንዲህ አይደለም ምሑሩም ህዝቡም ያልገባው አለ::ለውጡ በእዚህ መልክ ይሁን ሲሉ ተስቆባቸው ነበር::
የወታደራዊው መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት ሻምበል ፍቅረስላሴ በመፅሐፋቸው እንዲህ ንጉሱን ከቤተ መንግስት ልናወጣ ስንል ንጉሱ አሉን ያሉት "አልገባችሁም:" ነበር ያሉን ካሉ በኋላ ሻምበል ፍቅረስላሴ ከዓመታት በኋላ የፃፉት መፅሐፍ ላይ እንዳሉት::"ንጉሱ ያንጊዜ ትክክል ነበሩ::አዎን አልገባንም ነበር::" ብለዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ኢትዮጵያ በዘመነ የገጠማት ፈተና ምን ዓይነት እንደሆነ አልገባውም::
√ ለኢትዮጵያ የሚደክመውን ዓቢይን፣
√ የኃይለስላሴ ሃውልት መልሶ ያቆመውን ዓቢይን፣
√የጦር ኃይሉን በኢትዮጵያዊነት ለማደራጀት የሰራውን ዓቢይን፣
√ክልሎች ከማዕከላዊ መንግስት ድርሻ እንዳይኖራቸው ሆነው የተሰሩትን ሰብስቦ ቤለቤትነት እንዲሰማቸው ለማድረግ የደከመውን መሪ፣
√ የባሕር ኃይል መልሶ ለማሰልጠን የሚደክመውን ዓቢይ፣
√ የዓባይ ግድብ ከደረሰበት አቅንቶ ከአሜሪካ እስከ ግብፅ ሲወደርበት ግድቡን ከመ ሙላት ሌላ አማራጭ የለም ብሎ የጀመረውን ዓቢይ፣
√ ሽብርተኛው ሕወሃት ሰሜን ሸዋ ሲደርስ ለኢትዮጵያ እዘምታለሁ ብሎ የዘመተውና የተዘባረቀውን አመራር ወርዶ አስተካክሎ የእነሲኤንኤንን ድንፋታ ያስቆመ መሪን ዛሬ ደርሰው " ኢትዮጵያን ሊበትን ነው" የሚሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች አሉባልታ የሚያስተጋቡትን እንደ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ አልገባችሁም ብቻ አይበቃቸውም::ካልገባቸው ጋር ገብቷቸው ውሸትን ሥራዬ ብለው የያዙ ስላሉ::የገባው አውቆ ስም ሲያጠፋ ያልገባው እንደ 66ቱ አብሮ ስም ያጠፋል::ዐቢይ ታላቅ መሪ ነው::መለኪያህ ጀዋር ከሆነ ጀዋር ያለፈው አራት ዓመት መንግስት የሔደበት መንገድ ጥፋት ነው ብሏል::
የጀዋር ጥፋት የሆነ ለኢትዮጵያ ልማት ነው::አሁንም ያልገባችሁ አልገባችሁም::ዐቢይ ታላቅ መሪ ነው::
70 viewsGetachew Bekele, 18:45