Get Mystery Box with random crypto!

የጉብሬና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል 🇸🇦

የቴሌግራም ቻናል አርማ gubreahlelsunajemea — የጉብሬና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል 🇸🇦
የቴሌግራም ቻናል አርማ gubreahlelsunajemea — የጉብሬና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል 🇸🇦
የሰርጥ አድራሻ: @gubreahlelsunajemea
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-23 13:54:47 የእብድ ውሻ በሽታ እና መውሊድ

በዲን ላይ አዲስ አምልኮ (ቢድዓህ) ምንኛ መርዛማ በሽታ መሆኑን ከሚጠቁሙ ሀዲሶች አንዱ:
عن مُعَاوِيَةَ بْنِ أَبِي سُفْيَانَ ، أنه قَامَ حِينَ صَلَّى صَلَاةَ الظُّهْرِ، فَقَالَ : إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " إِنَّ أَهْلَ الْكِتَابَيْنِ افْتَرَقُوا فِي دِينِهِمْ عَلَى ثِنْتَيْنِ وَسَبْعِينَ مِلَّةً، وَإِنَّ هَذِهِ الْأُمَّةَ سَتَفْتَرِقُ عَلَى ثَلَاثٍ وَسَبْعِينَ مِلَّةً - يَعْنِي الْأَهْوَاءَ - كُلُّهَا فِي النَّارِ إِلَّا وَاحِدَةً، وَهِيَ الْجَمَاعَةُ، وَإِنَّهُ سَيَخْرُجُ فِي أُمَّتِي أَقْوَامٌ تَجَارَى بِهِمْ تِلْكَ الْأَهْوَاءُ كَمَا يَتَجَارَى الْكَلَبُ بِصَاحِبِهِ، لَا يَبْقَى مِنْهُ عِرْقٌ وَلَا مَفْصِلٌ إِلَّا دَخَلَهُ ". الحديث :مسند أحمد
حسنه الألباني: (صحيح أبي داود 4597 )

…የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ《 ሁለቱ የመፅሀፍ ባልተቤቶች እኮ በሀይማኖታቸው ወደ ሰባ ሁለት መንገዶች ተለያይተዋል። ይህችም ህዝብ እኮ ወደ ሰባ ሶስት መንገዶች ትለያያለች። አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ናቸው። አንዷም (የምትድነዋ) አልጀማዐህ ነች። እነሆ በኡማዬ (በህዝቦቼ) ውስጥ ልክ የእብድ ውሻ በሽታ በበሽተኛው ላይ እንደሚሰራጨው በሰውነታቸው ውስጥ እነዚህ ስሜቶች (ቢድዓዎች) የሚሰራጩባቸው ሰዎች ይወጣሉ። እርሱ ያልገባበት ደምስርም ይሁን መገጣጠሚያ አይተርፍም።》

የመውሊዱ ሰዎች

በቢድዓህ መርዙ ስለተመረዙ
በስሜት ተውጠው ሰክረው አየጦዙ
ከደማቸው ገብቶ ታስሮ ካጥንታቸው
በመውሊድ መፈንደቅ ውዴታ መስሏቸው
ውዴታና እብደት ተገላብጦባቸው
እንዳበደ ውሻ ሲያክለፈልፋቸው
መረጃ በሌላው ባዶው ጩሀታቸው
ጤነኛውን ሁሉ መንከስ አማራቸው
ሀዲሱን በተግባር በነርሱ አየነው

እናንተ ሆይ ንቁ መረጃ አድምጡ
ከባዶው ፈከራ ከስሜቱ ውጡ
ከቢድዓ ጥመት ከእሳት አምልጡ




ሸምሱ ( አቡ ሀመዊያህ)
http://t.me/Abuhemewiya
269 viewsedited  10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 08:16:53 عن أبي الجعد الضمري رضي الله عنه ،
أن رسول الله ﷺ قال :

((مَنْ تَرَكَ ثَلَاثَ جُمَعٍ تَهَاوُنًا بِهَا طَبَعَ اللهُ عَلَى قَلْبِهِ))

رواه أبو داود.
https://t.me/gubreahlelsunajemea
https://t.me/gubreahlelsunajemea
225 viewsedited  05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 07:35:05 سورة الكهف
ሱረቱል ከህፍ

قال رسول الله ﷺ
'' من قرأ سورة الكهف في يوم الجمعة أضء له من النور مابين الجمعتين''
==========~~~~~~~~~~~>

#በጁምዓ ቀን የቻልን ሱረቱል ከህፍንና ሌሎችም #በሀዲስ የፀደቁ ሱራወችን እንቅራ #ተጠቃሚዎች እንሆናለን።

መቅራት የማንችል ደግሞ ከውድ #ቃሪኦች እናዳምጥ በማዳመጣችን በርካታ #ጥቅሞችን እንጎናፀፋለን።
➲ አቀራራችን ይስተካከላል፤
➲ የሃርፍ አወጣጥ እንማርበታለን፤
➲ ቁርኣን ለመቅራት ያነሳሳናል፤
➲ ከዚህም በላይ ደግሞ የአላህን እዝነት እናገኝበታለን #ኢንሻአላህ

➲ ከታች سورة الكهف በተወዳጅ የአለማችን ቃሪኦች ቀርቦላችኋል። በስማቸው መሠረት እየገባችሁ አዳምጡ
=> አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን!!!

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
188 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 16:29:00 አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ

እነሆ እንደሚታወቀው ሸዋሮቢትን አቅጣጭታ የምትገኘው በኬሚሴ ዞን ውስጥ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጥቁሬ ቀበሌ የሚገኙት የአህለሱና ወልጀመዐ ማህበረሰቦች የመስጅድ ግንባታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ግሩፕ

  ታሪካቸውን በጥቂቱ

በዚች ቀበሌ በጣም ታዋቂ የሆነው የአህለሱና ወልጀምዐ ታጋይ
በዋነኝነት ሸይኽ ሙሀመድ ኑር ነው። ይህ ሸይኽ ዳዕዋውን ከጀመረ ከ20 አመት በላይ ሆኖታል። ነገር ግን ይች ሰፊ የሆነች ቀበሌ ጠንካራ በሆኑ ሱፍዮች እና አህባሾች የታጨቀች ነበረች ዳእዋውን አያደረገ በቀጠለበት ሰአት ይህንን የተውሂድ ጥሪ ካልተውክ ከእድር እናስወጣሀለን በማለት ዛቱበት ነገር ግን የእሱ መልስ እንዲያውም ከዚች ቡድንተኝነት ከበዛባት እድራችሁ ብወጣ እኔ ነኝ ተጠቃሚ የምሆነው ነበር ያላቸው በጣም ከሚያስገርመው ነገር የዚች ቀበሌ ቃዲ ነበር እስከዛች ሰአት ድረስ እነሱ ግን ይህም ሳይበቃቸው ልጅ ቢድር ማንም ሰው ቢሞትበት እሱን አንድ ሰው እንዳይረዳው በሚል ህዝቡ ላይ በቤተሰቦቹ ላይ ሴራ ቀጡ ይህም ሳይበቃቸው መሬቱንም እስከመቀማት ደረሱ ወደየት ይኬዳል ቢከስ ዳኞቹ እነሱ አሏሁል ሙስታዐን

➲ ይህም ሳይበቃቸው አሸባሪ ነው በማለት ብዙ ስቃይን አደረሱ ይህ ሁሉ ግን የነብያቶች ሱና መሆኑን ተረድቶ የተውሂድ ጥሪውን ቀጠለ ብዙ ሰለፍዮችንም አፈራ በሰርግ ሰበብ በሰደቃ ሰበብ ከሸዋሮቢት ፋርቃን መስጅድ ዳዒዎችን እየጠራ በዋነኝነት ኡስታዝ ሙሀመድ አሚንን እንዲሁም ከሰንበቴ፣ ከባልጭ ዳዒወችን በመጥራት ትልቅን ገድል ፈፀመ ሰለፍዮች እየበዙ ሲመጡ ቤት ተከራይተን ቂርአት እንዲሁም ጁሙዓ እስከማቋቋም ደረስን ነገር ግን ይህ ደስ ያላስባላቸው ሱፍዮች አሸባሪ ናቸው በሚል በ 2012 እስር ቤት ከተቱን የወረዳው ሀላፊ ቀበሌ ድረስ በመንጣት ህዝቡን ሰብስቦ ችግራቸው ምንድን ነው ብሎ ሀዝቡን ጠየቀ። ይህ የሱፍያ ማህበረሰብ ችግር ናቸው ብሎ ከቀጠፋቸው ከባባድ ውሸቶች

1 አልቃኢዳ ቡድን ናቸው
2 ዳኢ ብለው የሚያመጧቸው ሰወች በመኪና ሙሉ መሳሪያ ነው የሚያስገቡት
3 ዳእዋ እያሉ ሸዋሮቢት እና ባልጭ ሰንበቴ እየሄዱ አማራ እና ኦረሞን ያጣላሉ ምስክር  እነሱ አሏሁል ሙስታዓን እናም ወረዳው ትንሽ ሱና የሸተተው ስለነበር በተውሂድ ሰወች ላይ የሚያሴሩት ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ትንሽ ታስረው ተለቀቁ ከዚያም በገንዘባችን የተከራየነው ቤት ተዘጋብን ከዚያም ወረዳወቹ ያሉት ነገር ቢኖር ትንሽ እንኳ መስጅድ ሰርታችሁ ዳዕዋችሁን ቀጥሉ ነው ያሉት ትላንት በአንድ ሰው የጀመረው ዳዕዋ ሰለፍያ በዚች ቀበሌ ላይ ዛሬ በአሏህ ፍቃድ የተሻለ ለውጥ ይኖር ዘንድ የትም ቦታ የምትገኙ የተውሂድ ጉዳይ የሚያሳስባችሁ እህት ወንድሞቻችን ለዚህ የተውሂድ መስጅድ ስራ አሻራችሁን አሳርፉ በማለት ወደ ኸይር እንጠቁማችኋለን።

الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም በግልጽም የሚለግሱ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም፡፡


አቡል አባስ አሰለፍይ (ኑርየ አሊ አስፍው) ከሰለፊ ወንድሞቹ ጋር

አጠቃላይ እንቅስቃሴያችንን በሚከተለው ሊንክ ግሩፓችንን  በመቀላቀል ይከታተሉ!!!
      ➴➷➘➴➷➘
https://t.me/tikuremesgid
143 views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 13:51:39 የሙናፊቆች መንገድ የሸይጣን ነው

ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቁ

የከሰረው የፊትና ንግዳቸው

https://t.me/Abuhemewiya
225 viewsedited  10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 09:35:06 #ይድረስ_ለመውሊድ_አክባሪዎች
>

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው

የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያችን በቤተሰቦቻቸው  በባልደረቦቻቸው  ላይ  ይሁን


#ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም #የተወለዱበትን_ቀን_በፆም_ማሳለፋቸው_የሚጠቁመው_እኛም_በፆም_እንድናሳልፍ_እንጅ_ደግሰን_እንድንበላ_አይደለም_ፁሙ_ተብሎ_ታዞ_አይ_እኛ_እንበላለን_የምንል_ከሆነ_መቃረን_ነው_የሚሆነው_ምክንያቱም_ፆምና_ደግሶ_መብላት_ተቃራኒ_ናቸውና_ስለዚህ_መውሊድ_ነብዩን_ሶለሏሁ_ዓለይሂ_ወሰለም_መቃረን_እንጂ_ሱናቸውን_መከተል_አይደለም!!!

አመት  በመጣ ቁጥር ከሚያወዛግቡ ቢድዓዎች  ዋነኛው  መውሊድ (የነብዩ
#ሶለሏሁ_ዓለይሂ_ወሰለም የልደት በዓል)  ነው።  ይህ በዓል  ሊያወዛግበን  ወይም  ሊያጨቃጭቀን አይገባም  ነበር።  ለምን  ከተባለ ፦
መውሊድ  የዲን  አካል  ስላልሆነ፣
አላህ  ያዘዘው 
#በዓል_ስላልሆነ
መልዕክተኛችን አክብሩት ስላላሉን፣
ኹለፋኡ   ራሺዲን  
#ስላላከበሩት
አራቱ   ኢማሞች  
#ስላልተገበሩት
ሰባቱም ሙሃዲሶች ስለማያውቁት  እና ሌሎችም የዲናችን አካል እንዳልሆነ  የሚያስረዱ በመኖራቸው ምክንያት ነው።

አንድ ሀዲስ  ላስታውሳችሁ፦

  ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ""ኡመቶቼ ሁሉ ጀነት  ይገባሉ  እንቢ ያለ ሲቀር""  አሉ
  ""ማነው ጀነትን እንቢ የሚለው""  ተባሉ
""የታዘዘኝ ጀነት  ገባ።  ያመፀኝ (ትዕዛዜን  ያልተቀበለ) ደግሞ ጀነትን እንቢ  አለ""  አሉ

እስኪ 
#መውሊዲን  በዚህ  ሀዲስ  እንመዝነው፦

ረሱል ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም 
#የተወለዱበን ቀን  ፆሙ  እኛምን  እንዲንፆም  አዘዙን።
ልብ በሉ እኔን
#የታዘዘ ጀነት ገባ ነው ያሉት ስለዚህ የምንፆም ሰዎች #ታዘናል  ሱናቸውንም ተከትለናል።
ሌሎች ደግሞ
#መውሊድ የሚል ስም ሰጡትና #ደግሰው ሲበሉ ሲያበሉ  ይውላሉ

ልብ በሉ
#ነብያችን ﷺ ያሉት ፁሙ ነበር። እነዚህ (የመውሊድ  አክባሪዎች)  ግን አይ #አንፆምም እንበላለን እያሉ ነው።  በምላሳቸው ባይሉትም #የተግባራቸው  ትርጉም የሚያመለክተው ይህንን ነው።
ባጭሩ
#በግልፅ እየተቃረኑ ነው ያሉት  የሚቃረን ወይም የሚያምፅ ሰው ደግሞ  ከላይ ባየነው ሀዲስ #መሰረት ጀነት  አልገባም #እንዳለ ነው።

እኛ
#የምንላቸው ነገር ቢኖር #ጀነት  ከፈለጋችሁ ነብዩን ﷺ ተከተሉ
ነብዩ ﷺ በፆም
#አክብረውታል እያላችሁ ከምትበሉ ልክ እንደነብዩ ﷺ ከመብላት ተቆጠቡ ፁሙ!
ያልሰሩትን ሰርቼ
#ወዳጅ እሆናለሁ  ከምትሉ #የሰሩትን በመስራት #ወዳጅ  እሆናለሁ ብትሉ ህጋዊ (ሸሪዓዊ) ትሆናላችሁ።

አቡ ዒምራን አሰለፊ
           [ሙሐመድ መኮንን
]

https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
162 views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 19:07:45 አዲስ ተከታታይ እጥር ምጥን ያሉ ፅሁፎች
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

የፅሁፉ ርእስ፦ "መውሊድ እና የብዙ መርዞች እናት መሆንዋ"

የፅሁፉ ፀሀፊ፦ ወንድም ሙሀመድ አል–ወልቂጢይ

ፅሁፎቹን በተከታታይ በርእሳቸው ከስር እናስቀምጣለን ሊንካቸውን በመጫን ያንብቡ!

ክፍል አንድን ለማግኘት

"መውሊድ መች እና ማን ጀመረው?"
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed


ክፍል ሁለትን ለማግኘት
"መውሊድን የፈቀዱ ኡለሞች አሉን?"
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed


ክፍል ሶስትን ለማግኘት
"የመውሊድ ሰዎች ሚያመጧቸው ሹቡሀቶች እና ምላሾቻቸው"
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed


ክፍል አራትን ለማግኘት
"መውሊድ ውስጥ የሚገኙ መረረዞች በከፊሉ"
https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed


=======================
263 views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 17:23:31 ➢ አዲስ ወሳኝ ሙሓደራ

ርዕስ ☞ ኢስላም ከኛ ቡዙ ነገር ይጠብቃል

በሸይኽ አብዱልሐሚድ አልለተሚይ {ሐፊዘሁሏህ}

በአዳማ " አልፈትሕ ወ-ነስር " መድረሳ የተደረገ

• هدفنـا الدعـوة إلـى الله عزَّ وجـل بالرجـوع إلـى الكتـاب و السنـة  بفهـم سلـف الأمـة

https://t.me/Abdulham
252 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 10:07:13 መውሊድ እና የብዙ መርዞች እናት መሆኗ
≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈≈

መውሊድ ውስጥ የሚገኙ መርዞች በከፊሉ

①, ሽርኮችና ቢድአዎች

እንደሚታወቀው መውሊድ ብለው በሚያከብሩ በአል ውስጥ ብዙ ሺርኪያቶች እና ብዙ ቢድአዎች ይገኛሉ። ሽርክ አዘል የሆኑ ብዙ ውዳሴዎች፣ ሰለዋቶች፣ መንዙማዎች፣ ብትን ፅሁፎች ይነበባሉ።

②, ኢኽቲላጥ

በመውሊድ ውስጥ ከሚገኙ ተግባራቶችና ብላሽቶ መካከል ኢኽቲላጥ (የሴቶችና የወንዶች መቀላቀል) በከባዱ ይታያል። አብረው ተደባላቀው መብላት፣ መስገድ፣ መተኛት፣ መጨፈር፣ መቀመጥ ወዘተ…ብዙ ነገር በመደባለቅ ይሰራሉ። ግን የአላህ መልክተኛ ይህን ተግባረን በጥብቅ ከልክለዋል። ሰላት ውስጥ እንኳን የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይከለክሉታል። የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይህንን ያደረጉት የሴቶችንና የወንዶችን ቅርበትን ለማራራቅ ነው። ስለዚህ መውሊድ ለዚህ መንገድ መሆኑ እራሱ ክልክል ያደርገዋል። ከቢድአነቱ አልፎ።

③, ጭፈራ፣ ጫት፣ ኢስራፍ

ወንድሞችና እህቶች እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ በሸሪአአችን ጭፈራ፣ ጫት፣ ኢስራፍ እንዴት ይታያሉ?

ወላሂ ይገርማቹሀል እነዚህ ነገራቶች በአብዛኛው የመውሊድ ቦታዎች ላይ ይገኛሉ። ነገራቶቹ ሀራም ከመሆናቸውም ጋር። ኧረ መውሊድ ያመጣቸው መርዞች ብዙ ናቸው ለዚያ ነው ርእሴ "መውሊድ የብዙ መርዞች እናት" እዲሆን የወደድኩት። እና ባረከሏሁ ፊኩም ከቢድአነቱ አልፎ ለነዚህ መርዞች ሰበብ ሚሆን ከሆነ ሀራም ይሆናል።

④, ተሸቡህ

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ የራሳቹ የሆነ አላህ የወደደው ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የዘረጉት ለዱንያም ለአኼራም ሚጠቅም በቂ የሆነ ሀይማኖት አላቹ። ለምንድነው ቢድአ የሚሰራው? መጀመሪያ የተደነገገውንስ መቼ ጨረስን? ኧረ አላህን እንፍራ። በመቀጠል ደግሞ እንሚታወቀው ተሸቡህ( መመሳሰል) በሸሪአችን በጥብቅ የተከለከለ ነው። መውሊድ ደግሞ ነሳራዎች የኢሳ ልደት ብለው ከሚያከብሩት በአል ጋር መመሳሰል ተሸቡህ ነው። ስለዚህ ሀራም ይሆንብናል። እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ይህን መርዝ የመርዝ መአት የወንጀል ፌስቲባልን እንዋጋው። ትውልዱን ለማዳን ስንል ደግሞ ልጆቻችንም እናስጠንቅቅ።

አ በ ቃ ን

ሙሀመድ አል–ወልቂጢይ

https://t.me/abuzekeryamuhamed
https://t.me/abuzekeryamuhamed
295 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ