Get Mystery Box with random crypto!

መታገስ! ታላቅነት በአንድ ቀን አይገነባም! በአንድ ቅፅበት ሊፈርስ ግን ይችላል። የባቢሎን ግንብ | ❤️❤️ፍቅሬን በግጥም🌹🌹🌹🌹

መታገስ!

ታላቅነት በአንድ ቀን አይገነባም! በአንድ ቅፅበት ሊፈርስ ግን ይችላል። የባቢሎን ግንብን ለመገንባት አንድ ትውልድ ፈጅቷል፤ ለማፍረስ ግን ቀናት አልፈጀም።

እስከዛሬ የገነባኸውን ምርጥ ስብዕና እንድታጣ የሚያደርጉ ብዙ የሚያናድዱ፣ ራስህን እንድትጠላ፣ ተስፋ እንድትቆርጥ የሚያደርጉ ፈታኝ ነገሮች በየጊዜው ይገጥሙሀል። ማንነትህን የምታሳየው በሰላሙ ጊዜ አይደለም ከባዱን ወቅት ታግሰህ በማለፍ ነው እንጂ። አለበለዚያ ከዜሮ ትጀምራለህ!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ