Get Mystery Box with random crypto!

ገብርኤል መልአክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gebreal_abate — ገብርኤል መልአክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gebreal_abate — ገብርኤል መልአክ
የሰርጥ አድራሻ: @gebreal_abate
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.57K
የሰርጥ መግለጫ

መዝሙር
ስብከት
የተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መረጃዎች ያገኙበታል
ኦርቶዶክስ የአለም ሁሉ መዳኛ ናት
Join&share
ቻናላችንን ለመቀላቀል
@gebreal_abate
.group
@likee_melaek
ጥያቄ፣ሀሳብ እና አሐስተያየት ካሎት
@kedus_gebreal_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 23:53:24 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።  ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።  ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥  ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።  ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።  እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።  ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።  ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። 

ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። 

                          የዩሐንስ ራዕይ 13÷1-9


የ 666 ትርጉሙ ምንድ ነው

ማይክሮ ቺፕስ የሚባለውስ ምንድ ነው

የአለም ፍፃሜስ መቼ ነው

ስለ አለም ፍፃሜ የሚያትተው የራዕይ መፅሐፍስ ትርጉሙ ምንድነው

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
Ŝúbŝčŕibé our youtube channel











7 viewsመንፈሳዊ 0K, 20:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:11:58 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






27 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:36:37 #እውነት_የሞቱ_ወገኖች_ናቸው_የሚያናግሩን? ክፍል 2

በፍፁም አይደለም በአንድ ወቅት ንጉስ ሳኦል አይንዶር በምትባል ስፍራ ወዳለች አንዲት ጠንቋይ ቤት አመራ ንጉሡ ወደሷ ሲሄድ ልክ ዛሬ አንዳንዶች ተከናንበው ሰው እንዳያያቸው ተደብቀው እንደሚሄዱት ተከናንቦ ነበር ብዙ ነገሮች ታውቃለች የተባለችው ጠንቋይ ግን ማን እንደሆነ አላወቀችም በመጨረሻም ማንን ላስነሳልህ? አለችው እርሱም ነብዩ ሳሙኤልን አላት ጠንቋይዋም ይህንኑ አደረገች። ሳኦል ግን እንዳሰበው አልተጠቀመም (1ኛ ሳሙ27÷7)

ይህንን የመፅሀፍ ቅዱስ ንባብ ያነበቡ ሰዎች እንዴት ጠንቋይ ሳሙኤልን ከሞት ማንሳት ይችላል? ብለው ሊገረሙ ይችላሉ ።

እውነቱ ግን ጠንቋዩ ነብዩ ሳሙኤልን አስነስታው ሳይሆን ሳሙኤልን አስመስላ አምጥታ ነው ምክንያቱም ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ እስኪመስል ድረስ እራሱን የመለወጥ ችሎታ ኘለው።

ክፍል 3 ይቀጥላል ........

Join&share
ቻናላችንን ለመቀላቀል

@gebreal_abate
.group
@likee_melaek

ጥያቄ፣ሀሳብ እና አሐስተያየት ካሎት
@kedus_gebreal_bot
225 viewsYeab, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:22:37 #ሙታንን_መሳብ_በመናፍስቱ_አለም_(ኔክሮማኒስ) ክፍል 1

ዛሬ በአለማችን ላይ የዚህ መንፈስ ተጠቂዎች ብዙ ናቸው። ለምሳሌ በአሜሪካ ውስጥ 500 ዶላር በመክፈል የሞቱ ዘመዶቻቸውን የሚያነጋግሩ አሉ።

ይህንን የሚያደርጉት ባልታወቀ ምክንያት የሞተን ሰው ማን እንደገደለው ለማወቅ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ለሠው ገንዘብ ሰጥቶ ከሆነ ምን ያህል ገንዘብ ለሰው እንደሰጠ ይጠይቁታል። ከሞት እስከ 100 አመት ብቻ ነው የሚሰራው። የይህ አይነቱ አሠራር በእግዚአብሔር ዘንድ ፈጽሞ የተጣሰ እና የተወገዘ ነው። ዘዳ18÷9-14 "በአንተ ዘንድ ሙታን ሳቢ ፣ መናፍስት ጠሪ አይገኝ " እንደተባለ

ክፍል 2 ይቀጥላል .......

Join&share
ቻናላችንን ለመቀላቀል

@gebreal_abate
.group
@likee_melaek

ጥያቄ፣ሀሳብ እና አሐስተያየት ካሎት
@kedus_gebreal_bot
241 viewsYeab, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:18:45 ከመናፍቃን ጋር ፊት ለፊት ስንጋፈጥ ይጠቅመናል ያለውን ጥቂት ጥቅሶች


#የማርያም_ክብር_እና_አማላጅነት
#ሉቃ 1÷39-46
#2ኛ ሳሙ 6÷9
#ዮሐ 19÷25-28
#ኢሳ 60÷14

#የኢየሱስ_አማላጅ_አለመሆን
#ዮሐ 16÷29-33
#ዮሐ 6÷47-52

#የቅዱሳን_አማላጅነት
#1ኛ ቆሮ 6÷1-5
#መዝ 112÷6
#መዝ 31÷18
# 2ኛ ነገስት 2÷15
#ማቴ10÷40-መጨረሻ

#የፆም_አስፈላጊነት
#ማቴ 4÷1-5
#ማቴ 17÷18-22

#የፀበል_አስፈላጊነት
#ኢዮብ 38 ÷2
#2ኛ ነገስት 5÷1-19

#ስለ_መስቀል
#1ኛቆሮ 1÷18-20
#ማቴ 16÷24-27
#ሉቃ 14÷25-29

ለሌሎች ሼር በማድረግ ቤተሰብ እናብዛ
Join&share
ቻናላችንን ለመቀላቀል

@gebreal_abate
.group
@likee_melaek

ጥያቄ፣ሀሳብ እና አሐስተያየት ካሎት
@kedus_gebreal_bot
326 viewsYeab, 09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 12:18:45 ውድ የገብርኤል መልአክ ቤተሰቦች ለብዙ ተከታታይ ወራት ስለጠፋን በጣም ይቅርታ እየጠየቅን እንደቀድሞው ሀይማኖታዊ ነገሮችን ለማስተላለፍ ተመልሰናል
235 viewsYeab, 09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:09:13 ውዳሴ ማርያም

ውዳሴ ማርያም እጮኻለሁ
ድንግል እናቴን እጣራለሁ
እንደ አባ ኤፍሬም ነይ ባርኪኝ
ወድሰኒ ልጄ በይኝ

አዝ ……………

በሠርክ ጸሎት ላይ ውዳሴ ማርያም
ዜማ ስናደርስ ውዳሴ ማርያም
ድንግል ትመጣለች ውዳሴ ማርያም
በቤተመቅደስ ውዳሴ ማርያም
የብርሃን ምንጣፍ ውዳሴ ማርያም
ከፊቷ ተነጥፏል ውዳሴ ማርያም
ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ ውዳሴ ማርያም
ያመሰግናታል

አዝ ………………


አባ ሕርያቆስም ውዳሴ ማርያም
ምስጋና ያደርሳል ውዳሴ ማርያም
የቅዳሴው ዜማ ውዳሴ ማርያም
ልብን ይመስጣል ውዳሴ ማርያም
በጎ ነገር ልቤ ውዳሴ ማርያም
አወጣ እያለ ውዳሴ ማርያም
ዳዊት በበገናው ውዳሴ ማርያም
እየደረደረ

አዝ …………………

የንጽህናችን ውዳሴ ማርያም
መሠረት ነሽና ውዳሴ ማርያም
አንቺን ለማመስገን ውዳሴ ማርያም
ልቦናዬ ይብራ ውዳሴ ማርያም
ተፈሥሒ ድንግል ውዳሴ ማርያም
ኦ ቤተልሔም ውዳሴ ማርያም
ከአንቺ ተወለደ ውዳሴ ማርያም
መድኃኒዓለም

አዝ ………………

ቅዱሳኑ ሁሉ ውዳሴ ማርያም
ዙሪያሽን ከበዋል ውዳሴ ማርያም
አባ ጊዮርጊስም ውዳሴ ማርያም
ንዒ ድንግል ይላል ውዳሴ ማርያም
በወርቅ ዙፋን ላይ ውዳሴ ማርያም
ተቀምጠሽ ሳይሽ ውዳሴ ማርያም
ልቤ ተመሠጠ ውዳሴ ማርያም
ድንግል በግርማሽ

አዝ ……………

እልልልልልልልልልል
795 viewsYeab, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:09:12 #ምልክቴ_ነሽ

ምልክቴነሽ ድንግል ለሕይወቴ
በአንቺ ተፈታሁ ከእስራቴ
ቀና ብያለሁ አሁን ልጅሽ
ፀጋሽ ጎብኝቶኝ ቃልኪዳንሽ

+++++++++++++++++++++++
ተስፋ ያረኩት አልተበተነም
እምባዬ መሬት ከቶ አልወደቀም
ለበጎ ሆኗል ማልቀስ ማንባቴ
ሠላም ሠፈነ እልፍኝ በቤቴ
ቅኔ ነጠኩኝ የአባ ጊዮርጊስን
ቆምኩኝ ቅዳሴ የሕርያቆስን
የያሬድ ዜማ ሞላ በልቤ
የለም ወጀቡ ቀርባኝ መርከቤ

++++++++++++++++++++++++
ወገቤን ታጠኩ ጭንቀቴን ጥዬ
ዛሬስ በደስታ ይፍሠሥ እንባዬ
የሃዘን ልብሴን ድንግል ቀይራ
የደበዘዘው ሕይወቴ በራ
አራራይ ዜማ ዛሬ ተማርኩኝ
ፍቅሯ አሸነፈኝ እጄን ሠጠሁኝ
ቅኔ በልቤ ተመላለሰ
የድንግል ክብር ውስጤ ነገሰ

++++++++++++++++++++++
የዘረጋሁት እጄ ተሞላ
ማርያም ሆናልኝ ጥላ ከለላ
የውስጤ ፀሎት ዛሬ ሌላ ነው
የድንግል ክብር ምልጃው ቀየረው
ዛሬ ጎጆዬ አንፀባረቀች
ያማረ ሰንፔር ዕንቁ መሠለች
ቀንዴ ከፍ ከፍ አለልኝና
ሠዋው ለድንግል ይህን ምስጋና

Share and join

Group
@gebreal_abate



Channel
@likee_melaek



ለአስተያየት
@kedus_gebreal_bot
573 viewsYeab, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:09:11 #ኢ/ያ ናት ሀገሬ

ኢትዮጵያ ናት ሀገሬ
ተዋሕዶ ናት ክብሬ/×2/

ያደኩብሽ መሠረቴ
ተዋሕዶ ነሽ እናቴ
የአፌ መፍቻ ንግግሬ
ያሳደግሽ/2/ በዝማሬ

+++++++++++++++++

የፍቅር ሀገር ኢትዮጵያ
ዘውትር ምትይ ሀሌሉያ
አይበተን ሠላምሽ
አይታጎል/2/ ፀሎትሽ

+++++++++++++++++++

ቃል ገባሁኝ ላልክድሽ
እንዳልለይ ከእቅፍሽ
ደጅሽ ልኑር ጠዋት ማታ
ተዋሕዶ /2/ የኔ አሌንታ

++++++++++=+++++++++

ታሪከር አለሽ የሚነገር
በትውልዱ የሚዘከር
ትውፊትሽን ጠብቀሻል
ስሙን ይዘሽ /2/ አጊጠሻል

+++++++++++++++++

አይበጠስ ማህተቤ
የታተመ ነው በልቤ
አልፈልግም ሌላ ጥላ
እኖራለሁ/2/ ባንቺ ጥላ

+++++++++++++++++++++

የቅዱሳን ነሽ መፍለቂያ
የምስኪኖች መሸሸጊያ
እጆችሽን ወደጌታ
ምትዘረጊ/2/ ጠዋት ማታ

++++++++++++++++++++

ከቶ እንዴት ይሆናል አንቺን ብከዳሽ
ቀኜ ትክዳኝ ብዬ ቃል ገባሁልሽ
በደጀ ሠላምሽ ከቤትሽ አድጌ
አንቺማ ክብሬ ነሽ ሞገስ ማዕረጌ/2/

++++++++++++++++++++++++

በባዕድ ሀገር እንኳን ቢሆንም ሕይወቴ
መቼ ይለየኛል ማሕተቤ ካንገቴ
የክብርሽን እራስ ጌታዬን አምኜ
ላልተውሽ ቃል አለኝ በነፍሴ ጨክኜ/2/

Share and join

Group
@gebreal_abate



Channel
@likee_melaek



ለአስተያየት
@kedus_gebreal_bot
471 viewsYeab, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:09:08 ና በሠላም (3)
መድኀኔዓለም

ና በሠላም ከበጎቹ መሀል
ና በሠላም ስለጠፋው በግ
ና በሠላም ስለአንዱ ስለአዳም
ና በሠላም ስለ ሠው ልጅ ብለህ
ና በሠላም የሞትከው ጌታዬ
ና በሠላም ምንም ብበድልህ
ና በሠላም መሀሪ ነህና
ና በሠላም ይቅር በለኝ ባክህ
+++++++++++++++++++++++
ነይ በሠላም (3)
ድንግል ማርያም

ነይ በሠላም የሀገሬው ቅኔ
ነይ በሠላም የቅኔው አሻራ
ነይ በሠላም ከሚታፈስበት
ነይ በሠላም የቅኔው አዝመራ
ነይ በሠላም የነዲያን ሲሳይ
ነይ በሠላም የተማሪ እራቱ
ነይ በሠላም አንቺ አይደለሽም ወይ
ነይ በሠላም ድንግል አዛኝቱ
++++++++++++++++++++++++
ና ሚካኤል(3)
ምስለ ገብርኤል

ና ሚካኤል ቅድስት አፎሚያን
ና ሚካኤል ፈጥነህ የረዳሀት
ና ሚካኤል ክፉ አውሬ ዲያቢሎስ
ና ሚካኤል እንዳያሳድዳት
ና ሚካኤል እንደ አፎሚያ
ና ሚካኤል ስእልህን ይዘን
ና ሚካኤል እንለምንሃለን
ና ሚካኤል ፈጥነህ ድረስልን
+++++++++++/+++++++++++
ና ዑራኤል(3)
ምስለ ሩፋኤል

ና ዑራኤል የጥበብን ፅዋ
ና ዑራኤል ያጠጣህ ለእዝራ
ና ዑራኤል የጦቢትን አይኖች
ና ዑራኤል ፈውሰህ ያበራህ
ና ዑራኤል ከሊቀ መልአኩ
ና ዑራኤል ከሩፋኤል ጋራ
ና ዑራኤል ፈጥነህ ድረስልን
ና ዑራኤል አውጣን ከመከራ
+++++++++++++++++++
ና በፀሎት(3)
ተ/ሃይማኖት

ና በፀሎት ብራናው ሲገለጥ
ና በፀሎት ገድለ ተ/ሃይማኖት
ና በፀሎት ከሠው ልጅ ልቦና
ና በፀሎት ይወጣል አጋንንት
ና በፀሎት የቅዳሴው እጣን
ና በፀሎት ሲወጣ ከዋሻው
ና በፀሎት ምድርን ይባርካል
ና በፀሎት ፀሎተ ምህላው
+++++++++++++++++++++
ነይ በደመና(3)
እናት ቅድስት ሀና

ነይ በደመና ከታቦታት ሁሉ
ነይ በደመና ሃና ትለያለች
ነይ በደመና ከታቦታት ሁሉ
ነይ በደመና ሃና ትለያለች
ነይ በደመና የአምላክን እናት
ነይ በደመና በሆዷ ይዛለች
445 viewsYeab, 13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ