Get Mystery Box with random crypto!

#እንድታውቁት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስ | Fuad islamic calligraphy🤲

#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅ ተጓዦች ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የ2014 ዓ.ም የሐጅ ተጓዦች አጠቃላይ አገልግሎት ዋጋ 183 ሺህ 500 ብር መሆኑንም ምክር ቤቱ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር ያመለክታል።

ምክር ቤቱ የዋጋ ዝርዝሩን እና ብር የሚገባባቸው ባንክ እና ቁጥሮቻቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ሀጃጁ ባንክ ያስገባበትን ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አድርጎ በመያዝ ኦርጅናሉን ይዞ መምጣት እንደሚጠበቅበት ነው ያስታወቀው።

የሐጅ ተጓዦች ሊያሟሉ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ፦

1. ለሐጅ የሚሄደው ግለሰብ ከ65 ዓመት በታች የሆነ

2.የኮቪድ 19 ክትባት የወሰደ እና የማረጋገጫ ወረቀቱን የያዘ

3. የታደሰ ፓስፖርት ያለው፤ ፓስፓርት የሌለውና ጊዜው ያለቀ ከሆነ ወደ ጦር ሃይሎች ሆላንድ ኢምባሲ አጠገብ ዋናው ቢሮ በመምጣት ሂደቱን ማፋጠን ይችላል።

4. ባልና ሚስት አብረው የሚሄዱ ከሆነ የጋብቻ ማረጋገጫ ያስፈልጋል። ግዴታ ነው!

5. ልክ የዛሬ ወር በረራ ስለሚጀመር ቶሎ በመመዝገዝ ሂደቱን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚቻል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል።

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia