2022-05-23 05:59:32
(credited አብርሃም ፀ.)
ንባብ
-----
ከመጽሐፍ በብዙ የራቁ ሰዎችን አትመን ፤አውቀው ባይጎዱህ እንኳን ባለማወቅ ይገድሉሃል ወይም ያስገድሉሃል።
– Lemony Snicket
የአንድ ማኅበረሰብን ባህል ለማውደም ከተፈለገ መጻህፍትን ከማቃጠል ይልቅ የማያነቡ ትውልዶችን መፍጠር የበለጠ ወጤታማ መላ ነው።
– Ray Bradbury
ሰዎች ኢሞራላዊ ብለው የሚፈርጇቸው መጻሕፍት ካሉ የነዚህ መጻሕፍት ደራሲዎች የዓለምን ነውር እያጋለጡ እንደሆነ ጠርጥሩ።
- Oscar Wilde, The Picture of Dorian Gray
በአሁን ጊዜ ጸሎት ሊደረግላቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል አንዱና ዋንኛው የቴሌቪዥን መቀመጫ ቦታን በመጽሐፍ መደርደሪያ ስለመተካት ነው።
– Roald Dahl
ከመናገር በፊት ማሰብ ይገባል ቢባልም ከማሰብ በፊት ግን ንባብ ሊኖር ግድ ነው። ዓለማችን በበርካታ ረብ የለሽ ንግግሮች እየተወረረች ያለችውም በዚህ ምክንያት ነው።
- Fran Lebowitz
ሰዎች ሁሉ ተስማምተው በሳምንቱ ቀናት ላይ ለንባብ ብቻ የሚውል ስምንተኛ ቀን ሊጨምሩ ይገባል።
- Lena Dunham
ጥሩ መጻህፍትን ማንበብ ከቀደሙ ዘመናት ልሂቃን ጋር ቁጭ ብሎ እንደመጨዋወት ነው።
- Descartes
የማያነቡ ሰዎች ከዓለም የትናንትና ታሪኳ፣ ከነገ ሕልሟና ከዛሬዋ ማንነት የተገለሉ ባይተዋር ናቸው።
- John Green
ግራ ገብቶህ መወሰን ባቃተህ ጊዜ መላ ይዞ የሚደርስልህ ትናንት ስታነበው የኖርከው መጽሐፍ ነው።
- Oscar Wilde
መጻሕፍትን አንብበው ወደየትም ሥርቻ ወርውረዋቸው ሊሆን ይችላል፤ አኩርፈው ግን ጀርባ የሚሰጡ ወዳጅ አይደሉም። ዋጋ ከሰጧቸው ደግሞ የዘላለም አፍቃሪዎ ናቸው።
- John Green
@frombooks1234
꧁༻༒༺꧂
1.4K viewsዳኒ, 02:59