Get Mystery Box with random crypto!

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ | Free Education Ethiopia ✔️︎

የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የአሁኑ ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑን ከቀናት በፊት መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ በወረቀት ነው የሚሰጠው።

ይህ የፈተና አሰጣጥ አካሄድ በዩኒቨርሲቲዎች ላይ ፣ በመንግሥት በጀት ፣ በትምህርት ቢሮዎች ላይ ጫናውን እንደሚቀንስ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አመልክቷል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ ከወዲሁ ዝግጅቶቹ እየተደረጉ ሲሆን የሶፍትዌር ስራው ከወዲሁ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የዘንድሮውም ምዝገባ በኦንላይን ሲሆን፣ ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ ይሄዳል ተብሏል።

የተሻሉ የፈተና አዘጋጆች፣ ፈተናዎች እንዳይሰረቁ የሳይበር ጥበቃ፣ የደህንነት ካሜራዎች ፣ የተቋማት ትብብር (ኢንሳ፣ ፈተናዎች አገልግሎት) ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የፈተና ህትመት ዝግጅት ከዚህ ቀደሙም በተሻለ መልኩ ጠንካራ ስራ በጋራ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ እራሳቸውን ለመመዘኛ ፈተናው ብቁ እና ዝግጁ እያደረጉ መሄድ ያለባቸው ሲሆን መምህራን፣ ወላጆች፣ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተማሪዎችን እያገዙ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማደርግ አለባቸው።

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ገብተው ባለፉት ሁለት ብሄራዊ ፈተናዎች ማለትም በ2014 እና 2015 ከተፈተኑት አጠቃላይ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አምጥተው ያለፉት እጅግ ጥቂት ናቸው።

በ2014 ፈተና 896,520 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 30,034 ወይም 3.3 በመቶ ብቻ ሲሆኑ በ2015 ፈተና 845,099 ተማሪዎች ተፈትነው ማለፍ የቻሉት 27,267 ወይም 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው።

በተለይ ፈተናው በየአካባቢው ካሉ ትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ ወጥቶ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተመዘገበው ውጤት ብዙሃኑን ያስዳነገጠ እንዲሁም የትምህርት ስርዓቱ ያለበትን አሳሳቢ የሚባል ደረጃ ያመላከተ ሆኗል።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!