Get Mystery Box with random crypto!

ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተናው መብቶችና እና ግዴታዎች ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብ | Free Education Ethiopia ✔️︎

ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተናው መብቶችና እና ግዴታዎች

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።

ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።

በመጨረሻም የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት  የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል።

ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፍ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።

ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል።

ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።

ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል። ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም።

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው። ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።

ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም። ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።

ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።

ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

ማየት ለተሳነው እና ድጋፍ የሚሹ ተፈታኝ የፈተናውን ጥያቄዎች የሚያነብለትና የሚሰጣቸውን መልሶች የሚያጠቁርለት ፈታኝ በግሉ እንዲመደብለት ይደረጋል።

ተፈታኞች ፈተናውን ለመውሰድ የሚችሉት በቅድሚያ ትም/ቤት በተመዘገበበት ጣቢያ እንጂ የፈተና ጣቢያ ቀይረው ሊፈተኑ አይችሉም።


ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች

የግል ስልክ (Mobile phone)፣ታብሌት፣

የጆሮ ማዳመጫ (earphone) እና ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣

የእጅ ሰአት፣

ማንኛውም የግል ጽዳት ማስጠበቂያ ሆነ ማስዋቢያ ቁሳቁስ፣

ማንኛውም ዕቃ ለመያዣነት የሚያገለግል ቦርሳ/እቃም የያዘ ቦርሳ፣
ማንኛውም ስለት ነክ ነገርና ብረት

መልካም የፈተና ዝግጅት!

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!