Get Mystery Box with random crypto!

' የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል ' - ፕሮፌ | Free Education Ethiopia ✔️︎

" የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና  ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ልክ እንደባለፈው አመት በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን  አብራርተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!