Get Mystery Box with random crypto!

12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እስካሁን የሚሰጥበት ቀን ባይታወቅም ክልሎች ፣ ዞኖች ፣ ወረዳዎች ለፈተ | Free Education Ethiopia ✔️︎

12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እስካሁን የሚሰጥበት ቀን ባይታወቅም ክልሎች ፣ ዞኖች ፣ ወረዳዎች ለፈተናው ዝግጅት እያደረጉ ነው።

በተለይ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት እክል እንዳይፈጠር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ይሰማል።

ለአብነትም በአማራ ክልል የመቅደላ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለምንም ችግር ለማጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።

ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፅ/ቤት የዲሽ ተከላ ስራ መሰራቱን፣ በመብራት መጥፋት ፈተና እንዳይቋረጥ አስተማማኝ ጄኔሬተር መዘጋጁቱን ፣ የፈተና መፈተኛ ክፍሎች መብራታቸው በትክክል መስራቱን እንዳረጋገጠ እና ለፈተናው ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ፅ/ቤቱ ፈተናው በተለያዩ ምክንያቶች ወቅቱን ጠብቆ ባለመሰጠቱ በተማሪዎች ላይ መዘናጋት እና የስነ ልቦና ጫና ማሳደሩን ገልፆ ተማሪዎች ከዚህ ስሜት ውስጥ ወጥተው ከትምህርት ቤት ሳይርቁ ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ መልዕክት አስተላልፏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመፈተኛ ታብሌቶች ግዥ ተፈፅሞ ት/ቤቶች ላይ ከደረሰ በሗላ 2 ሳምንት የመለማመጃ ጊዜ እንደሚሰጥ እና ለዚህም ለተማሪዎች የICT ባለሙያዎች እገዛ እንድሚያደርጉላቸው ተገልጿል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!