Get Mystery Box with random crypto!

ዜና እረፍት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዮስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ | ፍኖተ ቅዱሳን አበው

ዜና እረፍት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዮስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንዲከናወን ሲኖዶሱ ወሰነ

የካቲት 25/2014 (ዋልታ) ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ እንዲከናወን ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ የካቲት 27/2014 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ውሳኔ ማሳለፉን ኢኦቴቢ ዘግቧል፡