Get Mystery Box with random crypto!

ጠቃሚ ምክሮች ① ለረጅም ጊዜ ብቻህን አትቀመጥ … ብቸኝነት እንድትተክዝና ድብርት ውስጥ እ | 🌹ፍቅር እስከ ጀነተል ፊርደውስ

ጠቃሚ ምክሮች


① ለረጅም ጊዜ ብቻህን አትቀመጥ … ብቸኝነት እንድትተክዝና ድብርት ውስጥ እንድትገባ ያደርግሀል… መልካም ሰዎችን ተቀላቀል።

② ሰላትን ከወቅቷ አታሳለፍ ።

③ ዚክሮችን አብዛ… አላህን በብዛት አስታውስ… አላህን ማስታወስ ልብን ያረጋጋልና።

④ አላህን መሃርታ ጠይቅ… ኢስቲግፋር ሪዝቅን ያሰፋል ፣ ነገሮችን ያግራራል ።

⑤ ለሰዎች ፊትህን ለቀቅ አድርግ… ውዴታቸውን ታገኛልህ ።

⑥ ራስህን ከሰዎች ጋር ማወዳደርን አቁም ።

⑦ በአላህ ላይ ያለህ እምነት ከፍርሀትህ በአጠቃላይ ሊበልጥ ይገባል።

⑧ አንድን ነገር ስህተት መሆኑን እየተጠራጠርክ አትፈፅም ።

⑨ እንደሚታወቀው ለውጥ የሚጀምረው አስተሳሰበን ከመቀየር ነው… ስለዚህ መጀመሪያ ውስጥህን ለመቀየር ስትሞክርና ስትችል መለወጥህ እርግጥ ይሆናል።

⑩ ውድቀትህን መፍራትና መጥላት የለብህም ። እንደውም ለወደፊት ስኬትህና ራስህን ለመለወጥ ምክንያት እንዲሆንህ ማድረግ አለብህ ።

⑪ የራስህን ስራ ለመስራት ስትፈለግ ራስህን ችለህ ለመስራት ጣር ። የራስህን ሀላፊነት ሌሎች ሰዎች እንዲወጡልህ አትጠብቅ ። ህልምህን ለማሳካት በማንም ሰው ላይ ጥገኛ አትሁን ። ህልምህ እውን የሚሆነው በራስህ ጥረት ብቻ ነው።

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@tolehaahmed
┗━ ━━━━ ━┛