Get Mystery Box with random crypto!

على هامان يا فرعون؟؟ ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ… ፊርዓውን ከነበረ | 🌹ፍቅር እስከ ጀነተል ፊርደውስ

على هامان يا فرعون؟؟
ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ…


ፊርዓውን ከነበረበት ድንበር ያለፈ ጥመት ጋ ጅል (ፋራ) ነገር ነበር አሉ። አማካሪው ሃማን ደግሞ እንደ የትኛውም የንጉሶች አማካሪ ብልጣብልጥ ነበር አሉ። እናም ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት በፊርዓው “የጌትነት ሙገታ” ያመነች አሮጊት ፍየልዋ ይሞትባትና ወደ ፊርዓውን ቤት ትመጣለች።

ስትመጣ ፊርዓውን አልነበረም ሃማንን አገኘችው።
"ጉዳይሽ ምን ነበር?" ሲላት
"ፍየሌ ሞታብኝ ፊርዓውን ሕያው እንዲያደርጋት ነበር የመጣሁት።" ትለዋለች

ሃማን ብልጥ ነበር; ብለን የለ?
"ነይ በቃ ፊርዓውን አሁን ግመል እየፈጠረ ስለ ሆነ ይቆይብሻል። ስለዚህ ሌላ ፍየል ልስጥሽ።" ይላትና ሌላ ፍየል ሰጥቷት ትሄዳለች።

ፊርዓውን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሃማን "አንዷ አሮጊት ፍየሏ ሙቶባት ሕያው እንድታደርግላት መጥታ ነበር።" ሲለው ፊርዓውን ደነገጠ።

ሃማን "አይዞህ! ፊርዓውን ግመል እየፈጠረ ነው። ብያት ሌላ ፍየል ሰጥቻት ሄዳለች። አትመጣም።" አለው።

በዚህ ጊዜ ፊርዓውን እንደ መረጋጋት አለና በረጅሙ ተንፍሶ…………
«ግመል መፍጠር እኮ እንዴት እንደ ሚያደክም ብታይ» አለው።


ሃማን ፈገግ አለና… …
على هامان يا فرعون
ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ አለው

በሃማን ላይ ሙድ ትይዛለህ ወይ እንዴ ጭራሽ ልትሸውደኝ ያምርሃል ማለቱ ነው።

ከዛኔ ጀምሮ ሰዎች በሚያውቁት ነገር ላይ ሊሸውዳቸው ለሞከረ ሰው
على هامان يا فرعون
ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ አለው

እያሉ አባባል አድርገው ይዘውታል።

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@tolehaahmed
┗━ ━━━━ ━┛