Get Mystery Box with random crypto!

እቀናለሁ አዎ አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡ አዎን እ | 💋የዲያሪ ላይ ጥቅሶች❤️


እቀናለሁ አዎ
አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡
አዎን እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡
ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ  ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
(እኔ ምን አቃለሁ
ብቻ ወድሻለሁ!!)