Get Mystery Box with random crypto!

#የልቤን_ሁሉ የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር እመቤቴ ሆይ ከአንቺ በቀር የደካማው ሰው መጠጊያ | የጃቴ ኪዳነ ምሕረት የፍኖተ ሰማዕታት ሰንበት ት/ቤት መዝሙር ክፍል

#የልቤን_ሁሉ

የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር
እመቤቴ ሆይ ከአንቺ በቀር
የደካማው ሰው መጠጊያ እኮነሽ
ሃዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ

ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ (2)
ከሲኦል ዓለም ስላመለጡ
ፃድቅ በስራው ያኔ ሲድን(2)
እጠራሻለሁ ድንግል አንቺን
#አዝ
የጭንቄ ደራሽ አክኪሌ ነሽ(2)
ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ
ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው (2)
በአዘ ንኩኝ ሠዓት እጠራሻለው
#አዝ
ዋሴ ነሽ ለእኔ ድንግል እናቴ(2)
ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነ ቴ
ሁልጊዜ ለእኔ በጎ የሆንሽ(2)
ምን ልበል ለአንቺ ቃላት የለኝ
#አዝ
ለአዘንኩኝ ለእኔ ደስታዬ ነሽ(2)
ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ
ስምሽ ሃጥአንን የሚቀድስ/
ከሞት ወደ ህይወት የሚመልስ
#አዝ
የመንገዴ ስንቅ የርሃቤ መርሻ(2)
ለታመመ ሰው ነሽ መፈወሻ
የተማጸነ በስምሽ አምኖ(2)
ማን አፍሮ ያውቃል አንቺን ለምኖ

#ዘማሪት #ፋንቱ #ወልዴ