Get Mystery Box with random crypto!

'...የሰው አሳብ መጨረሻ የሌለው ሰፊ ነገር ሲሆን ያሳብ መግለጫ የሆኑት ቃላት ግን በመዝገብ ይጠ | ፈላስፎች ምን አሉ❓

"...የሰው አሳብ መጨረሻ የሌለው ሰፊ ነገር ሲሆን ያሳብ መግለጫ የሆኑት ቃላት ግን በመዝገብ ይጠቀለላሉ። ከዚህ የተነሳ ሰው ላሳቡ ወሰን ያበጅለት ዘንድ አስፈላጊ ሆኖ ያገኘዋል። አሳብ የነፍስ ባህርይ ሲሆን ቃል የሥጋን ጠባይ የሚያሳይ ሆኖ ይገኛል። ነፍስ በሥጋ ውስጥ አድራ እንደምትገኝ አሳብም በቃል ውስጥ አድሮ ይኖራል። ነፍስ ሥጋን እንደምታንቀሳቅሰው አሳብም ለቃሎች ሕይወት ይሰጣቸዋል። ነፍስ ከሄደች በኋላ ሥጋ በድን እንደምትሆን ሁሉ አሳብም የተሰወረ ሲሆን ቃሎች በድን ሬሳ ይሆናሉ።..."



ምንጭ ፦ " ሥልጣኔ ማለት ምንድን ነች....ገጽ 16 "
ደራሲ ፦ ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል


ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል