Get Mystery Box with random crypto!

አመለጥከኝ ጓዴ አንደበቴ ታስሮ ቃላት ሳይተነፍስ፥ ከጎኔ ተገኝተህ እንባዬን ምታብስ፥ | 💞🌷ፍቅር እና Ⓛⓞⓥⓔ🌷💞

አመለጥከኝ ጓዴ

አንደበቴ ታስሮ ቃላት ሳይተነፍስ፥
ከጎኔ ተገኝተህ እንባዬን ምታብስ፥
የውስጤን ያንጀቴን የምትረዳልኝ፥
መልካም ሀሳቦቼን ይሁን የምትለኝ፥
ምርጡ ጓደኛዬ፤
እኔ ላንተ ሳልደርስ ሞቱ ቀደመብኝ።
፧ ፧ ፧
ድሮ ትዝ ይልሃል፤
በልጅነት እድሜ ባሳለፍነው ዘመን፥
ትምህርት ቤት ለመሄድ፤
ሁሌ ተጠባብቀን፥
ለጨዋታም ቢሆን ከቤት ተጠራርተን፥
በፍቅር በደስታ ጨዋታን ተጫውተን፥
በክረምት በጭቃው በበጋ ባቧራው፥
ዝናብና ፀሀይ ፍቅራችንን ሳይሽረው፥
ለኳስ ካለን ፍቅር፤
አሰልጣኝ ፈልገን ገንዘብ እያዋጣን፥
ከሰፈር ልጆች ጋር፤
ኳስ ስንለማመድ ከጫካ ውስጥ ሆነን፥
ከላይ ታች ሰፈሮች፤
ግጥሚያ እየተጋጠምን፥
አሳልፈናታል ያቺን መልካም ዘመን፥
በልጅነት ጮራ በፍቅር አንድ ሆነን።
፧ ፧ ፧
ትዝ ይልሀን ያኔ ገና በልጅነት፥
አቅማችን ሳይዳብር በህፃንነት ወቅት፥
አንተ አቅራቢያ ሆኜ፤
ድንገት ሰው ሲመታኝ፥
ማንም ይሁን ማንም፤
ሂደህ የምትመታልኝ፥
የሚያስፈራሩኝን፤
ከለላዬ ሆነህ ጋሻ የሆንክልኝ፥
እንዴትስ ይረሳል እነዛ ጊዜያቶች፥
የማንመልሳቸው አላፊ ትውስቶች።
፧ ፧ ፧
የዳበስናት ሂወት፤
ከጥሩውም ደስታ ከመጥፎው ትካዜ፥
ልርሳው ቢባል እንኳ፤
እንዴትስ ይረሳል ያሳለፍነው ጊዜ፥
ከሰፈር ልጆች ጋር አብረን ተሰባስበን፥
ፍጥር ቦሊቦሊ አባሮሽ ቴዘሩን፥
ሹሌና እሽኩሌታ፤
የህብረት ጨዋታውን፥
ፒቲና ኢላማ በብይና ፖስተር፥
አክሮባት ስፖርቱን፤
ማንጠባጠብ ሳይቀር፥
ገመድ እና ቃጤ፤
ሌሎችም ጨዋታ እንጫወት ነበር።
፧ ፧ ፧
ታድያ ምን ይደረግ፤
በዛች መርገምት ቀን በጥር መጀመሪያ፥
የተጠራህበት ሰዓት ደረሰና፥
በማይሆን ሰዓት ላይ፥
ከሞት መልአክ ጋር ተገናኛቹና፥
ባልታሰበ ጊዜ፤
ያለእድሜህ አመራህ ወደ ሞት ጎዳና፥
እኔ ግን ለአምላኬ ስላንተ እምለው፥
ሁል ጊዜ ከርሱ ጋር፥
በአፀደ ገነት ነፍስህ እንዲኖር ነው።

#በሱፍቃድ
ነፍስ ይማር
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
John Winsome