Get Mystery Box with random crypto!

ስነ ፍጥረት ክፍል (፯) ስድስት #የዕለተ_አርብ_ፍጥረታት #አርብ | ፍቃዱ ሲሳይ የተለያዩ መጣጥፎች፣ግጥሞች ፣ የአመታዊ ክብረ በዓላት ወረቦች እና ታሪካዊ ቦታዎች በምስል



ስነ ፍጥረት
ክፍል (፯) ስድስት

#የዕለተ_አርብ_ፍጥረታት

#አርብ፦የሚለው የሚለው የዕለቱ ስም አረበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው #መጨረሻ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር በዕለተ እሑድ ጀምሮ በዕለተ አርብ አጠናቋል።

#የአርብ ፍጥረታት 4 ናቸው።
1.ዘመደ እንስሳት
2.ዘመደ አራዊት
3.ዘመደ አእዋፋት
4.የሰው ልጅ (መዝ 139፥18)
መዝ 48፥12
ኦ.ዘፍ 1፥26
የሀሙሱ እና የአርቡ ፍጥረታት ልዩነት
#.የሀሙሱን ፍጥረታት ያስገኘው ውሃ ነው። ኦ.ዘፍ 1፥20
#.የአርቡ ፍጥረታት ግን ያስገኘችው ምድር ናት። ኦ.ዘፍ 1፥24

#የሰውን ልጅ ለምን መጨረሻ ፈጠረው?

መጀመሪያ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድሞ አዘጋጅቶ ሊፈጥረው ስለፈለገ

1.የሚመገበው፦እንስሳት እና አትክልት
2.ብርሐን የሚሰጡት፦ፀሐይ እና ጨረቃ
3.የሚጠብቁት፦ቅዱሳን መላዕክት
4. የሚኖርባት:- ምድር
5. የሚወርሰው:- ሰማያዊ ርስት

እነዚህ ሁሉ የግድ ያስፈልጉታል እና አዘገየው።
ከጎኑ ለምን ሄዋንን ፈጠራት?
1.ጎን የፈለገ እርቃን ቢኮን በልብስ ይሸፈናል። የባል እና የሚስት ገበናም በሰው ፊት አይወራም እና
2.እሷን ከጭንቅላቱ ከፍ አድርጎ ቢፈጥራት ኖሮ ትሰለጥንበት ነበር
ዝቅ አድርጎ ከቁርጭምጭሚቱ ቢፈጥራት ኖሮ አዳም ይነግስባት ነበር

ለዛ ነው መካከለኛውን ቦታ መርጦ ከዛ የፈጠራት። ሁለቱም እኩል መሆናቸውን ሲያሳይ ነው።

የጋብቻ አላማ ምንድን ነው?
1.ዘር ለመተካት
2.ከዝሙት ጠንቅ ለመራቅ
3.ለመረዳዳት

1ኛ ቆሮ 7 : 1 - 10

የመጨረሻው ክፍል

ክፍል 8 ይቀጥላል....

የእስካሁኖቹን የተለቀቁትን ክፍላት በደንብ አንብቡ በ 24 ሰዓት ውስጥ የሚመለስ ጥያቄ ይኖረዋል።