Get Mystery Box with random crypto!

ፀሀዩን ስንፈራ ተቃጠልን ብለን ዝናብም በጊዜው ጎርፍ ሆኖ ጨረሰን እቤቱ ይቅር በለን ራራልን ለእኛ | ትምህርተ አበው

ፀሀዩን ስንፈራ ተቃጠልን ብለን
ዝናብም በጊዜው ጎርፍ ሆኖ ጨረሰን
እቤቱ ይቅር በለን ራራልን ለእኛ
ከምድር አተናል ደገኛ እረኛ
ደማችን በምድር ፈሰስ እንደዋዛ
አምላክ ሆይ እግዘን ልብ እንድንገዛ
እማምላክ ምድርሽን ርስትሽን እያት
ካንቺ በቀር እኮ ተስፋ ምንም ያላት።

(በየቦታው በግፍ ለተገደሉት ወገኖቻችን ምህረትን ለሁላችን መጽናናትን የድሉን። ሰላማችንን ይመልስልን)

ዲ/ን ፍቃዱ ጎንፋ (ዘፍቁረእግዚእ)
ሰኔ 15/2014 ዓ.ም