Get Mystery Box with random crypto!

“ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ | ትምህርተ አበው

“ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።”
ራእይ 12፥1

ግንቦት 21 ቀን እመቤታችን ንጰጽሕይት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሰራች ቤተክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ በግልፅ ለአምስት ቀን መታየቷን እንዘክራለን።

በዚህም ሕዝብም አህዛብም ለአምስት ቀን ያክል ተመልክተዋታል ወደ ቤታቸው ሲሄዱም ትባርካቸው ነበር።

አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ሁላችንን ትባርከን እናትነቷ አማላጅነት ከሃገራችን ከኢትዮጵያ እና ከሁላችንም ጋር ይሁን።