Get Mystery Box with random crypto!

ኑር መስጂድን የፊታችን እሁድ እንረከባለን! የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ኑር መስጂድን የፊታችን እሁድ እንረከባለን!

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኑር መስጂድን የፊታችን እሁድ ይረከባል።


ታህሳስ 26/1015 ረቡዕ

በዛሬዉ እለት የሁከትና የብጥብጥ ጠንሳሹ አቶ መንሱር ዘይኑ አብዱልቃድር በመስጂዱ ቅጥር ግቢ ባደራጃቸዉ አካላት በስለት የታገዘ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን በሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል።

በትላንትናው እለትም በተመሳሳይ መልኩ ባደራጃቸው ወጣቶች ሁኩትና ብጥብጥብ ለማስነሳት መጣሩ ይታወሳል::

እንደሁልጊዜዉም ምዕመናን ተ ስፋ ለቆረጡ ዱርዬዎች መልስ ከመስጠት ይልቅ በሆደ ሰፊነት አሳልፏል።

ይህን ጉዳይ አልባት ለመስጠትም አቶ መንሱር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ፀጥታ ዘርፍ ቢሮ እንዲገኙ የተደረገ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ ጠቅላይ ም/ቤ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ከተደረገ ቡኃላ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በፃፈዉ ደብዳቤ መሰረት አቶ መንሱር ከኑር መስጂድ አስተዳደርነት መሰናበቱ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት የፊታችን እሁድ ታህሳስ 30/2015 እሁድ ከጠዋቱ 3:00 ላይ አቶ መንሱር ዘይኑ በተገኘበት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኑር መስጂዱን ይረከባል።

አቶ መንሱርን ጨምሮ ጭፋራዎቹ የርክክቡ  ቃል ጉባዔው በተያዘዉ ሰነድ ላይ ተስማምተዉ ፈርመዋል። የፀጥታ ዘርፍ በተገኘበትም እለተ እሁድ ርክክቡ ይፈጸማል።

Mujib amino



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia