Get Mystery Box with random crypto!

ታህሳስ 30/2015 የኑር መስጂድ አስተዳደር ርክክብ ይካሄዳል!!! በደብዳቤ ቁጥር 0044/15 | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

ታህሳስ 30/2015 የኑር መስጂድ አስተዳደር ርክክብ ይካሄዳል!!!

በደብዳቤ ቁጥር 0044/15 በቀን 20/3/2015 የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ሐጂ መንሱር ዘይኑን ከኑር መስጂድ አስተዳደርነት ያሰናበተ መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም በአስተዳደሩ በኩል ለማስረከብ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ርክክቡ ሳይፈፀም ቆይቷል።በዚህም የተነሳ ጉዳዩ የሁከትና ብጥብጥ ምክንያት ሆኗል።

በመሆን በዛሬው እለት የከተማዋ የሰላምና ፀጥታ አካላት ባሉበት የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች ከሐጂ መንሱር ዘይኑ ጋር ባደረግነው ህግ የማስከበር ውይይት ርክክቡ ታህሳስ 30/2015 ቀን የከተማውና የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ፣የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እንዲሁም ሐጂ መንሱር በተገኙበት እንዲከናወን በተፈረመ ቃለ ጉባኤ ስምምነት ላይ ተደርሶል!!!



https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia