Get Mystery Box with random crypto!

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!! ~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

በእርግጥም ለጋሽ መሆን ይከፍላል!!

~ ደስታን በልግስና ውስጥ ያገኙት የአለማችን ቁጥር አንድ በጎ አድራጊ፣

#Ethiopia | ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ይባላሉ:: ሳዑዲ አረቢያ ካፈራቻቸው ቢኒየነሮች መካከል አንዱ ናቸው:: ከንጉሳውያን ቤተሰብ ሳይሆኑ ቢሊየነር መሆን የቻሉ ሰው ናቸው:: በአለም ግዙፉን አልራጅሂ ኢስላማዊ ባንክ መመስረት ችለዋል::

በህይወታቸው ያጋጠማቸውን አንድ አስተማሪ ክስትተት እንዲህ ሲሉ ያካፍሉናል -

"በልጅነቴ እጅግ በድህነት ውስጥ ነው ያደኩት:: ቤተሰቦቼ ድሆች ነበሩ:: በአንድ ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪ እያለው ትምህርት ቤቱ የመዝናኛ ጉዞ ስላዘጋጀ በዚህ የሽርሽር ጉዞ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ 1ሪያል ማዋጣት እንደሚጠበቅበት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አስታወቀ:: እኔም በዚህ ጉዞ ላይ ለመሳተፍ እጅግ ስለጓጓው ለወላጆቼ አንድ ሪያል እንዲሰጡኝ እያለቀስኩኝ ጠየኳቸው:: ነገር ግን ወላጆቼ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወት የሚኖሩ ሚስኪኖች ስለነበሩ ይህን አንድ ሪያል ስለሌላቸው ሊሰጡኝ አልቻሉም:: የጉዞ ቀናት መቃረቡን ተከትሎ አንድ ሪያሉን የሚሰጠኝ በማጣቴ እጅግ በጣም አለቀስኩኝ ፤አዘንኩኝ::

ለጉዞ አንድ ቀን ሲቀረው በትምህርት ቤቱ የወሰድነው ፈተና ውጤት ደርሶ ስለነበር የፈተና ውጤታችንን ስንቀበል ከሌሎች ተማሪዎች የላቀ ውጤት በማምጣቴ ፍልስጤማዊ የሆነው መምህራችን ተደስቶብኝ በተማሪዎች ፊት አስጨብጭቦ ውጤቴን ሰጠኝ:: ለማበረታታም አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ አበረከተልኝ::

ለጉዞ መዋጮ የሚያስፈልገኝን አንድ ሪያል በሽልማት መልኩ በማግኘቴ እጅግ በጣም ተደሰትኩኝ:: ያንን የተሸለምኩትን ኣንድ ሪያልም ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በፍጥነት ሄጄ በመስጠት ብዙ በጓጓሁለት ጉዞ ላይ መሳተፍ ቻልኩኝ::

ለቀናት ሳነባ የነበረው እንባ በደስታ ተቀየረልኝ:: የቀናት ለቅሶዬ በዛች አንድ ሪያል ሽልማት የተነሳ ለረጅም ጊዜያት ውስጤ በቀረ ደስታ ተለወጠልኝ::

ጊዜያት ነጎዱ:: እኔም ትምህርቴን አጠናቀኩኝ:: ጠንካራ እና ታታሪ ሆኜም በስራ ዘርፍ ላይ ተሰማራው:: የአላህ ፀጋ ብዙ ነውና ስራዬን በረካ አደረገልኝ:: ፀጋውንም በኔ ላይ አንቧቧልኝ:: ከትንሽ ስራ ተነስቼ በሳኡዲ አረቢያ የመጀመሪያው የሸሪዓ መር ባንክ በመመስረት በመላው ሳኡዲ አረቢያ ቅርንጫፎች በዙልኝ::

በአንድ ወቅት በልጅነቴ ተማሪ እያለው አንድ ሪያል የሰጠኝ መምህሬን በማስታወስ በወቅቱ የሰጠኝ አንድ ሪያል ሽልማት ነው ወይስ እርዳታ ? በሚል ከእራሴ ጋር ሙግት ውስጥ ገባው:: እራሴን ደጋግሜ ጠየኩኝ:: ግን ፈፅሞ መልስ ላገኝለት አልቻልኩም::

መምህሩ ያንን አንድ ሪያል የሰጠኝ ምንም አስቦ ቢሆን ለእኔ ግን በወቅቱ የነበረብኝን ትልቅ ችግሬን ቀርፎ አስደስቶኛል ፤ ያንን የደስታ ስሜት ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም ስል ለራሴ ነገርኩት::

ውስጤ ለሚመላለሰው ትዝታ እና ጥያቄ ምላሽ ሊሆነኝ የሚችለው ይህን መምህር ካለበት አፈላልጌ አግኝቼው ስጠይቀው ነው በሚል ወደ ቀድሞ ትምህርት ቤቴ በመሄድ ፍልስጤማዊ መምህሬን ማፈላለግ ጀመርኩኝ::
በአላህ እገዛ መምህሬ ያለበትን ቦታ አፈላልጌ ማግኘት ቻልኩኝ:: እሱን ለማግኘትም ቀድሜ ተዘጋጀሁና ወዳለበት ስፍራ አቀናው::

ፍልስጤማዊው መምህሬ በጡረታ ላይ ሆኖ፣ እጅግ በድህነት እና በችግር ላይ ሆኖ አገኘውት::

የእርሱ ተማሪ እንደነበርኩኝ በማብራራት እንዲያስታውሰኝ አደረኩት ::

የተከበርከው ውዱ መምህሬ ሆይ ፣እኔ እኮ ለረጅም አመታት የቆየ ያንተ ባለእዳ ነኝ አልኩት::

አንድ ደሃ ሰው ምን የሚያበድረው ነገር ኖሮት ነው የማበድርህ ሲል ተገርሞ ጠየቀኝ::

እኔም ተማሪ እያለው በውጤቴ ምክንያት የሰጠኝን አንድ ሪያል አስታወስኩት::

መምህሬም :- ክስተቱን በማስታወስ እየሳቀ ባለእዳ ነኝ ያልከኝ ታዲያ አሁን ያቺን አንድ ሪያል ልትከፍለኝ ነው ? በማለት ተገርሞ እየሳቀ ጠየቀኝ::

እኔም አዎ ውዱ መምህሬ በማለት መለስኩለት::

ወደ መኪናዬ እንዲገባ በማድረግ እጅግ ዘመናዊ መኪና በግቢው ውስጥ የቆመበት ግዙፍ ዘመናዊ ቪላ ቤት ውስጥ ይዜው ገባው::

መምህሬ ሆይ ተማሪ እያለው ለሰጠኸኝ አንድ ሪያል ምላሽ ባይመጥንም፤ ይሄ ግዙፍ ቪላ እና መኪና ላንተ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀሁት ነው፤ በህይወት ዘመንህም የሚበቃህን ያህል ገንዘብ እኔ ዘንድ ተዘጋጅቶልሀል ብዬ ነገርኩት::

መምህሬ እጅግ በመደንገጥ ይሄ ፈፅሞ ለእኔ አይገባም፣ ይህ በጣም ከልክ ያለፈ ብዙ ነው በማለት አይኑ በእንባ ተሞልቶ መቀበል እንደሚከብደው ነገረኝ:::

መምህሬ ሆይ በወቅቱ አንድ ሪያል ስትሰጠኝ የነበረኝ ደስታ ዛሬ አንተ ይህን ቪላ እና መኪና ስታገኝ ከተሰማህ ደስታ በላይ ነው:: የዛኔ የነበረኝ የልጅነት ደስታ እና ሀሴት ዛሬም ድረስ አይረሳኝም በማለት ለመምህሬ ስጦታዬን አበረከትኩለት::ይላሉ

በመጨረሻም ሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ ምክር ሲመክሩ

"ምን ጊዜም ለሌሎች ደስታን ፍጠር፣ የሌሎችን ጭንቀት አሶግድ ፣ ምንዳህን እጅግ ከሰጪው ፣ከለጋሹ እና ከደጉ ጌታ ጠብቅ ይላሉ'

ለመረጃ ያህል

ሼይኽ ሱለይማን አልራጅሂ ያላቸውን ሀብት ግማሹን ለልጆቻቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ግማሹን ደግሞ ለበጎ አድራጎት አበርክተዋል::

በአለማችን ታሪክ ግዙፉ የተባለለትን እና በአለም ድንቃ ድንቅ መዘገብ ላይ ሊሰፍር የቻለ ለበጎ አድራጎት አገልግሎት የሚውል በሳኡዲ አረቢያ በቀሲም ግዛት የሚገኘውን 5466 ሄክታር ስፋት ያለው የእርሻ ማሳቸውን፤ ይህም የእርሻ ማሳ በአመት 10ሺህ ቶን የቴምር ፍሬ የሚሰጥ እና በውስጡም 45 አይነት የተለያዩ የተምር ፍሬዎችን የያዘ፣ 200,000 የሚሆን የተምር ዛፍ ለበጎ አድራጎት ይውል ዘንድ ወቅፍ ማድረግ የቻሉ ሰው ናቸው::

ሸይኽ ሱለይማን አራጅሂ ለዳእዋና ለበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ቋሚ ድጋፍ እንዲሆን ወቅፍ ያደረጉት ካፒታል አሁን ላይ 60 ቢሊዮን ሪያል ደርሷል። ይህ በአለማችን እስካሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ወቅፍ ነው::

ሼይኹ ወቅፍ ካደረጉት የተምር እርሻ የሚገኘው የቴምር ምርት ተሽጦም ገቢው ለበጎ አድራጎት ማህበራት የሚከፋፈል ሲሆን ቀሪው ተምርም ለሁለቱ ቅዱሳን መስጂዶች መካ እና መዲና ለሚገኙት ሀረሞች የረመዳን ኢፍጣር ፕሮግራም አገልግሎት ይውል ዘንድ ለምዕመናን በነፃ ይከፋፈላል::

በሳዑዲ አረቢያ ባሉ ከተሞች ላይ በሼይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ እና ቤተሰባቸው አማካኝነት መስጂድ እና መድረሳ ያልተገነባበት ከተማ ማግኘት ያዳግታል:: በሁሉም ቦታዎች ላይ መስጂዶችን አስገንብተዋል::

በስራቸው ላለው ሰራተኞቻቸውም ደሞዛቸውን ወሩ ከመጠናቀቁ በፊት በመክፈል ይታወቃሉ::

ሽይኽ ሱለይማን አል ራጅሂ በአንድ ወቅት ቃለመጠይቅ ሲደረግላቸው

ግማሹን ሀብታችሁን ለቤተሰባችሁ፤ ግማሹን ደግሞ ለወቅፍ ለግሰውታል:: ለራስዎት የግል ወጪ የሚሆንስ ምን አስቀምጠዋል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ

ውብ በሆነ ፈገግታ ተሞልተው "ባጭሩ ምላሼ ምንም ነው!" የምለብሳቸው ልብሶች ብቻ እኔ ጋር አሉኝ:: እድሜዬ በሰማኒያዎቹ ውስጥ ነኝ! ከዚህ ቡኃላ ምን ልፈልግ እችላለሁ? የወቅፍ ፕሮጀክቴ ወጪዬን ይሸፍናል፣ መጠለያ፣ ምግብ፣ ህክምና እና መጓጓዣ አገኛለው::በትንሹ ለመኖር በደንብ የተብቃቃው ነኝ:: ሲሉ መልሰዋል::

” ቢሊየነር ሆነው ግን ምንም ገንዘብ የሌለው ሰው በመሆኖት! "ምን ይሰማዎታል?" ሲባሉም