Get Mystery Box with random crypto!

#አስደሳች_ዜና የተፍሲር ደርስ ጅምር ተብለው ከሚጠቀሱ መሳጂዶች ዋነኛዋ ከሆነችው ከፈትህ አባቦ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

#አስደሳች_ዜና

የተፍሲር ደርስ ጅምር ተብለው ከሚጠቀሱ መሳጂዶች ዋነኛዋ ከሆነችው ከፈትህ አባቦራ መስጂድ የደስደስ ይዘን መተናል ለአመታት በሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን ይሰጥ የነበረው ተፍሲር ሀገራችን ላይ በነበረው ነባራዊ ሁኔታ እንደተቋረጠ ይታወቃል ከሳቸው ቡሀላም በሸይኽ አብዱል ሀሚድ እንዲሁም በኡስታዝ ባህሩ ኡመር ቀጥሎ የነበረ ቢሆንም በኮሮና እና በመሰል ሰበቦች መቀጠል አልቻለም ነበር።

እነሆ አሁን በአዲስ መልክ በአዲስ መምፈስ በሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን ዘወትር ሀሙስ ከመግሪብ እስከ ዒሻ ከፋቲሀ ጀምሮ ደርሱ ይጀምራል። አደራ እንዳያመልጥዎ።
እኔስ አመለጠኝ መምጣት አልቻልኩም ሰፈሬ ሩቅ ነው አልያም ሀገር ወስጥ አይደለሁም ብለውም አይጨነቁ ለናንተም በቀጥታ ስርጭት በፈትህ አባቦራ መስጂድ የፌስቡክ ገፅ መከታተል የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!!!


ለኢስላም እየሰራን ኢስላምን እንኑር!!!
የፈትህ አባቦራ መስጂድ የቂርአትና የዳዕዋ ዲፓርትመንት።

@fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia