Get Mystery Box with random crypto!

የሐጅ የመጨረሻ ተጓዦች ትላንት ለሊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይጓዙ መደረጉ ተገለጸ .. ሀሩ | ፈትህ አባቦራ መስጂድ

የሐጅ የመጨረሻ ተጓዦች ትላንት ለሊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይጓዙ መደረጉ ተገለጸ
..
ሀሩን ሚዲያ፥ ሰኔ 28/2014
..
የሐጅ የመጨረሻ ተጓዦች ትላንት ለሊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይጓዙ መደረጉ ተገለጸ። የሳኡዲ አየር መንገድ ሁጃጆቹን ይዞ የሄደ ሲሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትኬት የቆረጡ ተጓዦች ግን መጓዝ አትችሉም በሚል መከልከላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
..
በብዙ ውጣ ውረድ የተገኝን እድል አየር መንገዱ በሐጅ ቪዛ ተጓዦችን ማጓጓዝ ጊዜው ስላለቀ ማሳፈር አልችልም ያለ ሲሆን የሳኡዲ አየር መንገድ ግን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ሰዓት ቡሃላ ከለሊቱ 9ሰዓት በነበረው በረራ የመጨረሻ ሁጃጆቹን አሳፍሯል።
..
ትላንት ለሊት ኢትዮጵያ አየር መንገድ አላሳፍርም ያላቸው ሀጃጆች ቁጥር እስከ መቶ የሚደርሱ ናቸው። ሁጃጆቹ አየር መንገዱ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እዛው አድረው እየጠበቁ ይገኛሉ።
..
ሀሩን ሚዲያ


https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia