Get Mystery Box with random crypto!

ነጌሌ አርሲ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰንበት ትምህርት ቤት(FelegeGenet Sunday School)

የቴሌግራም ቻናል አርማ felegegenet_sunday_school — ነጌሌ አርሲ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰንበት ትምህርት ቤት(FelegeGenet Sunday School)
የቴሌግራም ቻናል አርማ felegegenet_sunday_school — ነጌሌ አርሲ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰንበት ትምህርት ቤት(FelegeGenet Sunday School)
የሰርጥ አድራሻ: @felegegenet_sunday_school
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 256
የሰርጥ መግለጫ

የነጌሌ አርሲ ደ/ል/ቅ/ጊ/ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰ/ት ቤት
ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት በ@felegegenetbot ሊንክ ያድርሱን
@felegegenetbot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-26 14:10:47
272 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 10:53:32
295 views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 16:25:47
179 views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 11:03:47 ✞ወጸቢሖ ተማከሩ✞

ቀዳማዊው አዳም ሕግህን በመጣስ
ከገነት ቢሰደድ ባሕርይው ቢረክስ
ዳግማዊው አዳም ክብሩን ልትመልስ
በነግህ ፈረዱብህ በአውደ ጲላጦስ

ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኵናን

ሦስት ሰዓት ሲሆን ቆመህ በአደባባይ
ጀርባህን ተገረፍህ አየህ ብዙ ስቃይ
ስለኃጢአት ቆሰልክ ስለበደል ታመምክ
ፍጥረትን በሙሉ ከደዌ ነፍስ ፈወስክ

ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ

ስድስት ሰዓት ሲሆን ልትውል በመስቀል
እጅህ ተዘረጋ ቀኖትን ሊቀበል
ከእርግማን በታች ያሉትን ልታድን
በመስቀል ተሰቀልህ የዓለሙ መድኅን

ጊዜ ሰደስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማእከለ ክልኤ ፈያት
     
ጥማችንን ልትቆርጥ ተጠማሁ በማለት
መራራ ሐሞት ጠጣህ ጌታ ማየ ሕይወት
የሕያዋን አምላክ ሲሆን ዘጠኝ ሰዓት
ስለ ሁላችን ሞትክ እንዲቀርልን ሞት

ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ገአረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ

ሙስና መቃብር እንዳናይ ልጆችህ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘው ቀበሩህ
በሠርክ ሲዖል ስትወርድ ነፍሳት ነጻ ወጡ
በሞት ጥላ ያሉ ወደ ብርሃን መጡ
282 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 11:01:21 በሕማማት የሚጸለዩ ፀሎቶች ምን ምን ናቸው?
በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም
የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ?

የሕማማት ጸሎት

በሕማማት የሚጸለየው በአብዛኛው ውዳሴ ማርያም እና መዝሙረ ዳዊት፤ የነቢያት ጸሎት ሲሆን የጌታን መከራ መስቀል የሚያነሱ መጻሕፍት ይጸለያሉ፡ ሕማማተ መስቀል፣ ድርሳነ ማሕየዊ የመሳሰሉ። መልክአ መልኮች፣ ድርሳናትና ገድላት የማይጸለዩት ዋናውን ጸሎት በጌታ ሕማማና መከራ መስቀል ለመስጠት ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ንባብ (ግብረ ሕማም) ዋናው የጸሎት ክፍል በመሆኑ ያንንም መሳተፍ ትልቁ ጸሎት ነው።

ጥብጠባ

በሰሙነ ሕማማት እለተ ዓርብ ስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሰሩትን ይናዘዛሉ ካህናቱን በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡

ይህ በስቅለተ ቀን የሚፈጸም ስነ ስርዓት ሲሆን ጥብጣቤ ማለት ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም የጌታን ግርፋት ያሳያል።፡ሕዝብ ክርስቲያኑ በእለተ ስቅለት ሲሰግድ ሲጸልይ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ ይሆናል። አርብ ከ 11 ሰአት በኋላ ስግደት እንደሌለ ግብረ ሕማሙ "አልቦ ስግደት "ይላል።

በሕማማት ወቅት የሚሰሙ የምንላቸው ከሌላ ቋንቋ የተወሰዱ ቃላት ትርጉም

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

"ኪርያላይሶን"

ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ “ኪርዬ ኤሌይሶን” ነው፡፡ “ኪርያ” ማለት “እግዝእትነ” ማለት ሲሆን “ኪርዬ” ማለት ደግሞ “እግዚኦ”ማለት ነው፡፡ ሲጠራም “ኪርዬ ኤሌይሶን” መባል አለበት፡፡ ትርጉሙም “አቤቱ ማረን” ማለት ነው፡፡ “ኪርያላይሶን” የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው “ዬ”ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ “ኤ” በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረው ነው፡፡

"ናይናን"

የቅብጥ(ጥንታዊው የግብጻውያን ) ቃል ሲሆን ትርጉሙ “መሐረነ፣ ማረን” ማለት ነው፡፡

"እብኖዲ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “አምላክ” ማለት ነው፡፡ “እብኖዲ ናይናን” ሲልም “አምላክ ሆይ ማረን” ማለቱ ነው

"ታኦስ"

የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ “ጌታ፣ አምላክማለት ነው፡፡ “ታኦስ ናይናንማለትም “ጌታ ሆይ ማረን” ማለት ነው፡፡

"ማስያስ"

የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ “መሲሕ” ማለት ነው፡፡ “ማስያስ ናይናን” ሲልም “መሲሕ ሆይ ማረን” ማለት ነው

"ትስቡጣ"

ደግ (ቸር) ገዥ ማለት ሲሆን "ትስቡጣ ናይናን" ማለት ቸር ገዥ ማረን ማለት ነው።

"አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ” ማለት ነው፡፡

"አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን “ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው

"አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ"

የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ፤የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን” ማለት ነው፡፡

የ41 ስግደት ምን እየተባለ ነው የሚሰገድ?

አንድ ክርስቲያን በፆም ጊዜ ከፀሎት በኋላ የጌታን መከራና ለእኛ ያሳየውን ፍቅር እያሰበ ከሐጢያቱ ብዛት ከአምላኩ ይቅርታ ያገኝ ዘንድ 41 ጊዜ እንዲህ እያለ ይስገድ

12 ጊዜ ---- #እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- #በእንተ እግዝዕትነ ማርያም መሐረነ
ክርስቶስ
12 ጊዜ ---- #ኪራላይሶን (አቤቱ ማረን)
5 ጊዜ ---- #ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ፣ ሮዳስ (አምስቱ የጌታ ችንካሮች)

✞ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
✞ አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ
✞ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር
✞ በፍስሐ ወበሰላም::


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE
✧┈┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈┈✧
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
@Z_TEWODROS
•✥• @Z_TEWODROS •✥•
✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
135 views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 09:49:26
204 views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 09:45:41 https://vm.tiktok.com/ZMLbNNdX6/
328 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ