Get Mystery Box with random crypto!

✞ወጸቢሖ ተማከሩ✞ ቀዳማዊው አዳም ሕግህን በመጣስ ከገነት ቢሰደድ ባሕርይው ቢረክስ ዳግማዊው አዳ | ነጌሌ አርሲ ደብረ ልዳ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ፈለገ-ገነት ሰንበት ትምህርት ቤት(FelegeGenet Sunday School)

✞ወጸቢሖ ተማከሩ✞

ቀዳማዊው አዳም ሕግህን በመጣስ
ከገነት ቢሰደድ ባሕርይው ቢረክስ
ዳግማዊው አዳም ክብሩን ልትመልስ
በነግህ ፈረዱብህ በአውደ ጲላጦስ

ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኵናን

ሦስት ሰዓት ሲሆን ቆመህ በአደባባይ
ጀርባህን ተገረፍህ አየህ ብዙ ስቃይ
ስለኃጢአት ቆሰልክ ስለበደል ታመምክ
ፍጥረትን በሙሉ ከደዌ ነፍስ ፈወስክ

ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ

ስድስት ሰዓት ሲሆን ልትውል በመስቀል
እጅህ ተዘረጋ ቀኖትን ሊቀበል
ከእርግማን በታች ያሉትን ልታድን
በመስቀል ተሰቀልህ የዓለሙ መድኅን

ጊዜ ሰደስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማእከለ ክልኤ ፈያት
     
ጥማችንን ልትቆርጥ ተጠማሁ በማለት
መራራ ሐሞት ጠጣህ ጌታ ማየ ሕይወት
የሕያዋን አምላክ ሲሆን ዘጠኝ ሰዓት
ስለ ሁላችን ሞትክ እንዲቀርልን ሞት

ጊዜ ተሰዓቱ ሰዓት ገአረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ

ሙስና መቃብር እንዳናይ ልጆችህ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘው ቀበሩህ
በሠርክ ሲዖል ስትወርድ ነፍሳት ነጻ ወጡ
በሞት ጥላ ያሉ ወደ ብርሃን መጡ