Get Mystery Box with random crypto!

ከኮሩ ክፍሎች ለመጡ የጤና ሙያተኞች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ረዳትነት ትምህርት እየተሰጠ ነው። | FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ከኮሩ ክፍሎች ለመጡ የጤና ሙያተኞች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ረዳትነት ትምህርት እየተሰጠ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም     
    
የኮሩ የጤና ክፍል ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል መኮነን ሞላ  መደበኛ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ረዳት ሰልጣኞች የሰራዊቱን ጤንነት ለመጠበቅ ለተልዕኮ አፈፃፀም እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ተላላፊና ተላላፊ የልሆኑ ወረርሽኝ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ቀድሞ ለመከላከል ታስቦ እየተሰጠ ያለ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገሪቱ የጤና ፖሊሲ መሠረት የመከላከያ ጤና ዋና መመሪያ የጤና ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸውን ሙያ እንዲጨብጡ በማድረግና ያወቁትን ዕውቀት በሰራ ላይ ማዳበር እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ የሚሠጠው ሙያዊ ሥልጠና ተገቢ መሆኑንም አሥረድተዋል።

ለሠራዊቱ ቀልጣፋ የህክምና እርዳታ ለመስጠትና በተለይም ደግሞ የቅድመ በሽታ መከላከል ስራዎችን በተገቢው ለመስራት ሠልጣኝ የጤና ሙያተኞች ከነባር የጤና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
 
ዘጋቢ ሱራፌል መልሰው
ፎቶ ግራፍ ሱራፌል መልሰው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official