2024-05-13 12:43:34
ህብረብሔራዊነታችንን በማጠናከር ለሁሉም የምትመች ሀገር እንገነባለን በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ በሊበን ጭቋላ ወረዳ ተካሄደ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 05 ቀን 2016 ዓ.ም
በምስራቅ ሸዋ ዞን በሊበን ጭቋላ ወረዳ በመከላከያ ሠራዊቱ እና በጥምር የፀጥታ ሃይሉ የሰፈነውን ሰላም እናፅና ለሰላማችን ዘብ መሆን ያለብን እኛው ነን፤ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፤መከላከያ ሠራዊቱ መስዋዕትነት እየከፈለ የሚያረጋግጠውን ሰላም ማስቀጠል የእያንዳንዱ ማህበረሰብ ሃላፊነት ነው ሲሉ የምስራቅ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አት አባቡ ዋቆ ገልፀዋል ።
ይህንን ሰላም ለማረጋገጥ ፅሀይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸው የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ህይወታቸውን እየገበሩ ላሉ ለመከላከያና ለመላው የፀጥታ ሃይሎቻችን ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የክፍለጦር ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሳሊወን ክብረሃሰን በበኩላቸው አካባቢውን ሰላም ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራን ቆይተናል ፤ አሁንም ወደፊትም መስዋዕትነት እየከፈልን የህዝባችንን ሰላም ለማረጋገጥ ላፍታም ቢሆን አንዘናጋም ፤ አሸባሪው ሸኔም እጁን ካልሰጠ በገባበት እየገባን እናጠፋዋለን ሲሉ ተናግረዋል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ ነጉ የወረዳው ነዋሪዎች የሰላሙ ባለቤት እኔው ነኝ ከሰላሙ የምጠቀመው እኔው ነኝ በማለት ለዚህ ኮንፍረንስ መሳካት ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነው ለተግባሩም ሁሉም በቅንነት መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።
ዘጋቢ አባተ ወልደእየሱስ
ፎቶ ግራፍ ጥላሁን አለሙ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
5.8K views09:43