Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ሰራተኞች ቅሬታ እና የድርጅቱ ምላሽ #FastMereja ኢትዮ ቴሌኮም የሽያ | FastMereja.com

የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ሰራተኞች ቅሬታ እና የድርጅቱ ምላሽ
#FastMereja
ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ክፍል ሰራተኞች ከሚያዝያ 14/2015 ጀምሮ ማደያ በመገኘት ነዳጅ ለሚቀዱ ደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ይሁንና አንድን ሰራተኛ ያለ ሽፍት እንዲሁም ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ በአስገዳጅ ሁኔታ ከጠዋት 12:30—2:00 እየሰራን እንገኛለን" ሲሉ ቅሬታቸውን ለፋስት መረጃ ገልፀው ነበር የሰራተኞቹን ቅሬታ ይዘን የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ክፍል ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑትን ፋስት መረጃ አነጋግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል

«ይህ ልዩ ፕሮግራም ህብረተሰቡን ለመደገፍ እና የመንግስትን አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራን ያለነው፣ አዎ እውነት ነው ሁላችንም ከስራ ሰዓት ውጪ እየሰራን ነው ያሉት ኃላፊው ግን በማስገደድ ሳይሆን የትርፍ ሰአት ስራ ለሚሰሩት ማንኛውም ሰራተኛ የትርፍ ሰአት ክፍያ እንደሚከፈል ቃል ገብተናል።» የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

@fastmereja