Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን ያለው ውጥረት የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ | FastMereja.com

በሱዳን ያለው ውጥረት የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሷል

በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ሚሊሻ አባላት መካከል እየተደረገ ያለው የተኩስ ልውውጥ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በካርቱም ሰማይ ላይ የጦር ጀቶች ሲበሩ ታይተዋል።

ሄምቲ በሚለው ቅጽል ስማቸው በሚታወቁት በጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል፣ ወደ አገሪቱ ጦር ስለሚቀላቀልበት ሁኔታ አንዲሁም ኃይሉን ማን ይመረዋል በሚለው አለመግባባት ተፈጥሮ ባለፉት ቀናት ውጥረት በአገሪቱ ውስጥ ሰፍኖ ነበር።

ዛሬ ቅዳሜ ከረፋድ ጀምሮ የተኩስ እና የፍንዳታ ድምጽ በመዲናዋ ካርቱም እየተሰማ ነው። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የካርቱም ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ተቆጣጥሪያለሁ ብሏል።

የአገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑም ተዘግቧል።

በዚህ መካከል የሱዳን ሠራዊት ናቸው የተባሉ የጦር ጀቶች በካርቱም ሰማይ ላይ ሲበሩ ታይቷል።

ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ በሱዳን የተከሰው ውጥረት እና ግጭት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ነው ታስነበበው።

@fastmereja