Get Mystery Box with random crypto!

በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ፤ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲለቀቁ ኢሰመኮ አሳ | FastMereja.com

በሚዲያ ጥፋት የተጠረጠሩ ታሳሪዎች በሙሉ፤ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲለቀቁ ኢሰመኮ አሳሰበ

በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት ተፈጽሟል በተባለ ወንጀል የተጠረጠሩ ታሳሪዎች “በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ከእስር እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰበ። የመንግስት የጸጥታ አካላት በፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና አባላት፣ በሚዲያ አባላት እንዲሁም በማህበረሰብ አንቂዎች ላይ ካተኮረ “እስር እና ማዋከብ” እንዲቆጠቡም ኮሚሽኑ ጠይቋል።

ኢሰመኮ ይህንን ማሳሰቢያ የሰጠው፤ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችን እና አባላትን “ዒላማ በማድረግ” እየተፈጸመ ያለን “እስር እና ወከባ” አስመልክቶ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 7፤ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው። በእነዚህ አካላት ላይ እየተፈጸመ ያለው “እስር እና ወከባ በእጅጉ አሳሳቢ” መሆኑን በገለጸው ኮሚሽኑ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ስምንት ጋዜጠኞች እና አንድ የማህበረሰብ አንቂ ለእስር መዳረጋቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

መረጃው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

@fastmereja