Get Mystery Box with random crypto!

የአባይ ሚዲያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም አሉ! ለበርካታ አመታት አባይ ሚዲያ | FastMereja.com

የአባይ ሚዲያ ጋዜጠኞች እና ሰራተኞች ደሞዝ አልተከፈለንም አሉ!

ለበርካታ አመታት አባይ ሚዲያ በሚል የዩቲዩብ ስያሜ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎችን እና ትንታኔዎችን ለተመልካቾች ሲያደረስ የነበረው አባይ ሚዲያ ካለፉት ሁለት አመት ጀምሮ በቴሌቪዥን ቻናል በመምጣት በይበልጥ በመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ እያተኮረ ያለው ሚዲያው አሁን ላይ ለሠራተኞቹ ከ ሶስት እስከ አራት ወር ደሞዝ መክፈል እንዳልቻለ አንዳንድ የጣቢያው ሠራተኞች ለፋስት መረጃ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ፋስት መረጃ በጉዳዩ ላይ የሚዲያው ኃላፊዎችን በስልክ አነጋግረን ነበር "በአካል ቢሮ ካልመጣችሁ በስልክ ማብራሪያ አንሰጥም" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

@fastmereja