Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊ | FastMereja.com

የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ 10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የመከላከያ ሠራዊት አስታወቀ

የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ዛሬ ረፋድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የጁንታው አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በዚህም የመከላከያ ሠራዊት የህወሓት ጁንታ አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙነትን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ በአካባቢው ለሚያገኘው የመከላከያ ሠራዊት አባል በአካል በመቅረብ አልያም በመከላከያ ወራዊት የስልክ ቁጥሮች መጠቆም እንደሚቻል ተገልጿል።
Via: EBC

-------------
@fastmereja