Get Mystery Box with random crypto!

ታላቅ ይቅርታ '5 ጉዳይ' በተሰኘው መፅሀፌ ላይ ሰፊ ሽፋን ያገኘው 'የባሮ ቱምሳ ገዳይ ማነው?' | FastMereja.com

ታላቅ ይቅርታ
"5 ጉዳይ" በተሰኘው መፅሀፌ ላይ ሰፊ ሽፋን ያገኘው "የባሮ ቱምሳ ገዳይ ማነው?" የሚለው ክፍል ብዙ የደበዘዙ እና የተሸፈኑ ታሪኮችን የገለጠ እና የእውነት ክር ብትቀጥንም እንደማትበጠስ ያሳየ በብዙ ልፋት እና ድካም የተዘጋጀ ስራ ነው::

ሆኖም ግን ይህ በታሪክ የምርምር ሰነድነት ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ፅሁፍ፤ ስነፅሁፋዊ ለዛ እንዲኖረው በማሰብ የመግቢያ ክፍል ሲሰናዳለት የመፅሀፌ አርታዒ አንድ አንቀፅ ቃል በቃል እና እንደወረደ ከደራሲ ሄኖክ በቀለ "ሀገር ያጣ ሞት" የተሰኘ መፅሀፍ ስረአተ ነጥብም ሆነ የህዳግ ማስታወሻ ሳይጠቀም እንዳለ ገልብጦ ተጠቅሟል::

ይህ ተግባር መፈፀሙን ያወቅሁት ዛሬ ማለዳ የወንድም ሄኖክን ቅሬታ ካነበብኩ በኃላ ነው:: በተፈፀመው ጉዳይ በተለይም ደግሞ እንደ አንድ ፀሀፊ ይህ ጉዳይ ምን ያህል አስከፊ መሆኑን ስለምረዳ ምንም እንኳን በስልክ ከሄኖክ ጋር ስለተፈጠረው ስህተት አስረድቼው የተግባባን ቢሆንም፤ ደራሲ ሄኖክን በአደባባይ ይቅርታ ማለት እፈልጋለሁ:: ከይቅርታ ባለፈም በቀጣይ ህትመት ላይ አንቀፁ በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ ተቀምጦ በህዳግ ምንጩ ተጠቅሶ እንዲወጣ ለማድረግ ቃል እገባለሁ::

በድጋሚ ለተፈጠረው ስህተት በሙሉ ሀላፊነቱን ወስጄ አንባቢዎቼን በሙሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ::

ቤተልሔም ታፈሰ!