Get Mystery Box with random crypto!

ኤርትራዊያን በእስራኤል ዉስጥ በፈጠሩት ግጭት አንድ ሰዉ መሞቱ ተሰማ በደቡብ ቴል አቪቭ በኤርትራ | FastMereja.com

ኤርትራዊያን በእስራኤል ዉስጥ በፈጠሩት ግጭት አንድ ሰዉ መሞቱ ተሰማ

በደቡብ ቴል አቪቭ በኤርትራ መንግስት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ስደተኞች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው በስለት ተወግቶ መሞቱን ፖሊስ እና የህክምና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል።

የማጌን ዴቪድ አዶም አምቡላንስ አገልግሎት እንደገለጸው በግጭቱ ሌሎች አምስት ሰዎች ቆስለዋል ያለ ሲሆን ሶስቱ በከፋ ሁኔታ ዉስጥ እንደሚገኙ ገልጿል። ፖሊስ ግጭቱን ተከትሎ ከ20 የሚበልጡ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቆ በነፍስ ግድያ የተጠረጠረውን ግለሰብ እያጣራ  መሆኑም ተዘግቧል።

ቀደም ሲል በእስራኤል እና በሌሎችም የአዉሮፓ ሀገራት በኤርትራውያን ስደተኞች መካከል ተመሳሳይ ሁከት ሲፈጠር ታይቷል። ይህም ማለት ባለፈው መስከረም በቴል አቪቭ ውስጥ ቢያንስ 170 ሰዎች እና የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ የተጎዱበትን ከፍተኛ ግጭት እንተጠበቀ ሆኖ እንደማለት ነዉ።

በተጨማሪም በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በደቡብ ቴል አቪቭ በመሰል ጥቃት ስደተኛ ለገዥው የኤርትራ መንግስት ደጋፊ ነበረች የተባለች ሴት በስለት መገደሏ ተነግሯል። በተመሳሳይ በናታኒያ አንድ ኤርትራዊ በስደተኞች መካከል በተደረገው ግጭት በጦርነቱ ተወግቶ ተገድሏል። በዚህ ሁካታ ዘጠኙ ተጎድተዉ አንድ ሰው በከባድ ቆስሎ ነበር ሲል ብስራት ሬዲዮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
****
ትክክለኛው የቴሌግራም ገጻችን ይህ ነው
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja