ክረምቱ መጥቶ ወደ ሰማይ ሽቅብ አንጋጥቼ ስመለከት የጠቆረው ዳመና ልቤን ያስታውሰኛል ጭጋጉንም ሳይ ኅጢአት ያጠለሸው ልቤ ፊቴ ላይ ድቅን ይላል ከዛ ደግሞ እርጥበቱ ሞልቶ የዝናብ ነጠብጣቦች ሲወርዱ በንስሀ ልብ ያፈሰስኳቸውው እንባዎቼ ትዝ ይሉኛል ለጥቆም ዝናቡ ሲያበቃ የጠቆረው ዳመና ቀለል ብሎ ሳየው ከንስሀ በኃላ የሚሰማኝን እረፍት ያስታውሰኛል ከሰዓታት በኋላ ግን መልሶ ሰማዩም ይጠቁራል የእኔ ልብም እንዲሁ። በዚህ የማያልቅ ዑደት ውስጥ ኅጢአቴ ደጋግሞ በብርድ አንዘፈዘፈኝ ግን የሚያሞቀኝ አንድ ፅኑ ተስፋ አለኝ በዚህ ውጥንቅጥቅ ውስጥ እንኳን አቅንቶ የሚያቆመኝ። "እሄዳለው ወደዛች ሀገር ወደ በጉ ከተማ" የሚል ፅኑ ተስፋ ብርድም ሙቀትም ወደ ሌለበት ክርስቶስ ብቻ ወደሚያበራበት ሀገር በእሱ ወደሚደምቀበት ደመና እና ጭጋግ ክረምት እና በጋ ቀን እና ማታ ፍፁም ወደ ሌለበት ወደ በጉ ከተማ ልሄድ እጅግ ናፍቄአለው በቃ የኅጢአት ደመና ልቤ ላይ አይደምንም እንዴት ደስ ይላል! Macarthur አንዴ እንዲህ ብሎ ነበር "መንግስተ ሰማይን ሳስብ የሚያጓጓኝ በወርቅ የተለበጡት በእንቁ የተዋቡት መንገዶች ሳይሆኑ የኅጢአት አለመኖር ነው" የእኔም ጉጉት ይሄ ነው ኢየሱስ ቶሎ ና 38 viewsAbrahamggrace, 04:37