Get Mystery Box with random crypto!

እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የ | Excellence Life Faith Church

እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። (የማርቆስ ወንጌል 11፥24)

ዓለም "ማየት ማመን ነዉ" የሚል ተፈጥሮአዊ የእምነት ትርጓሜ አላት። ይህም በመዳሰስና በመዳበስ የሚገኝ የስሜት እምነት ነዉ። እንደዚህ አይነቱ የስሜት እምነት፣ ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ ቶማስ የተመላለሰበትና ክርስቶስም ያወገዘዉ ተፈጥሮአዊ እምነት ነዉ።

የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር እዉነት ነዉና፣ እዉነትም የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ነዉና፣ ስለ እምነትም እዉነት የሆነዉ ቃለ እግዚአብሔር የሚናገረዉን መስማት በጣም ተገቢ ነዉ።

ክርስቶስ ብፁህ ናቸዉ ብሎ ያለዉ ሳያዩ ያመኑትን እንጂ አይተዉ ያመኑትን አይደለም። በዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት፣ በማመን የሚገኝ ማየት እንጂ በማየት የሚገኝ ማመን እንዳልሆነ እንረዳለን።

ከእግዚአብሔር የተቀበሉትም ሆነ የሚቀበሉት በቁስ ደረጃ እጃቸዉ ሳይገባ በእምነት ግን እንደ ተቀበሉ እርግጠኛ ሆነዉ የኖሩት ናቸዉ።

አንድ የቤት ባለቤት፣ ስለቤቱ ጉዳይ ቤቱን ማሳየት ሳይጠበቅበት የቤቱን ካርታ ካሳየ ታማኒነት እንደሚኖረዉ ልክ እንደዝያዉ በነገሮቻችን ፈንታ የነገሮቻችን ምንጭ የሆነዉን የእግዚአብሔርን ቃል ማሳየትና በቃሉም እዉነት ላይ መጽናት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ነው ::