Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር ሲመዘን የሰዉ ልጅ ህይወት ዋና ክፍል ፍቅር ነው ሰዉን በአምሳ | Excellence Life Faith Church

ፍቅር ሲመዘን

የሰዉ ልጅ ህይወት ዋና ክፍል ፍቅር ነው
ሰዉን በአምሳሉ የፈጠረዉ እግዚአብሔርም ፍቅር ስለሆነ፤ በምድር ላይ እንድንማረው የተፈለገው፣ ከሁሉ የሚበልጠውን ፍቅርን ነዉ :: ስለሆነም ፍቅር ጌታ ,ለሰጠን ትእዛዛቶች ሁሉ መሰረት በመሆኑ <<ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ተጠቅልሏል ይኸውም "ባልጀራህን እንደራስህ ውደድ የሜል ነው።"ገላ 5:-14 በውነቱ ራስ ወዳድ ሳይሆኑ ሌላን መውደድን መማር እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም ፤ምክንያቱም ራስ ወዳድነት የተፈጥሮ ባህሪያችን ስለሆነ፤ለዚህም ነው ከራስ አልፎ ሌሎችንም ለመውደድ ዕድሜያችንን ሁሉ የምንማረው ትምህርት ሆኖ የተሰጠን።ለዓለም በቀላሉ የሚታየው የህይወት ምስክርነታችን(ምሳሌነታችን)የዶክትሪን አቋማችን ወይንም ሌላ የሐይማኖት ስርአታችን ሳይሆን፤እርስበርስ ያለንን ፍቅር መሆኑን ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ብሏል<<እርስበርሳችሁ ብትዋደዱ ሠወች ሁሉ የእኔ ደቀመዝሙር መሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።ዮሐ 13:-35>>ከአስርቱ ትእዛዛት አራቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግኑኙነት ሲያመለክቱ ስድስቱ ግን ከሠወች ጋር የሚኖረንን ግንኙነቶች ናቼው። በእውነቱ ይህንን ትልቅ ሀሳብ ለመዘርዘር ጌዜ ያንሳል ቢሆንም ግን ባጭር ቃል ለመናገር አስሩንም ግንኙነቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ዋና የሆነውን ነገር በሁለት አረፍተነገሮች አጠቃሎቴል ""እግዚአብሔርን መውደድ""
""ሠወችንን መውደድ ""
<<ጌተ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል>> ይህም ባልንጀራህን እንደራስህ (እንደነፍስህ)ውደድ የሜለው ነው።ማቴ 22:-37-40ትእዛዛቶች ሁሉ በእነዚህ ሁለት handle(ማንጠልጠያ)እጀታ ተይዘዋአል።እግዚአብሔር መንፈሳዊ እድገታችንን ከሚመዝንበት አንዱ መንፈሳዊ ስርአታችንን ሳይሆንእግዚአብሔርን መውደዳችንን እና ባልንጀራችንን እንደራሳችን የምንወድበት ህይወታችንን ነው።