2022-03-15 16:49:35
አላህ የረሳቸው እንስሳት
---------------
“አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ ከነሱም በአራት ላይ የሚሄድ አለ። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡” (ሱራ 24:45)
በዚህ ጥቅስ መሠረት እንስሳት በአጓጓዛቸው ላይ ተመሥርቶ በሦስት መደባት ተከፍለዋል፦ በሆዱ የሚሄድ፣ በሁለት እግሮች የሚሄድና በአራት እግሮች የሚሄድ። ሌሎቹስ እንስሳት ለምን አልተጠቀሱም? አላህ የሚያውቀው እነዚህን ብቻ ነውን? ምናልባት ሙስሊም ወገኖቻችን አላህ እነዚህን ብቻ መርጦ መጥቀስ ስለፈለገ ነው ይሉናል። ይህ ግን የማያስኬድበት አንድ ምክንያት አለ። ከኡሥማን ቅጂ ጋር ተፎካካሪ የነበረው የኡበይ ቢን ካዕብ ቅጂ የተለየ ንባብ እንደነበረው በእስላማዊ ምንጮች ውስጥ እናነባለን።
ተፍሲር አልቁርጡቢ ይህንን አንቀጽ በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦
The walking on the belly is for snakes and fish and the likes of worms and others. Upon two feet is for humans and birds when they walk. Upon four is for all other animals. In Ubayy’s (copy of the) Qur'an: “and of them who walks upon more”. Hence in this addition he included all animals such as crab, however this is a copy of the Qur'an which did not gain consensus.
https://www.altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=5&tSoraNo=24&tAyahNo=45&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1
“በሆድ ላይ መኼድ ለእባቦችና ለዓሳዎች እንዲሁም ለትሎችና ለሌሎችም ነው። በሁለት እግሮች ላይ መኼድ ለሰዎችና ወፎች ነው። በአራት ላይ መኼድ ለሁሉም እንስሳት ነው። በኡበይ የቁርኣን ቅጂ ውስጥ፡- “ከእነርሱም ከዚህ በላይ በኾኑት ላይ የሚራመዱ አሉ ይላል። ስለዚህ በዚህ ጭማሪ ውስጥ እንደ ሸርጣን (ክራብ) ያሉ እንስሳትን ሁሉ አካቷል፤ ነገር ግን ይህ የቁርኣን ቅጂ መግባባት ያላገኘ ነው።”
የኡሥማን ቁርአን በኡበይ ቁርአን ውስጥ የነበረውን ዓረፍተ ነገር በመቀነሱ ምክንያት አላህ ሌሎቹን እንስሳት የረሳ አስመስሏል። በዚህ ሁኔታ “ቁርአን አንድ ነው፤ ምንም መለዋወጥ አልደረሰበትም” የሚለው የሙስሊሞች አሰልቺ መፈክር ቦታ የለውም።
4.7K views13:49