Get Mystery Box with random crypto!

ሱፊዩ ማህበረሰብ ኡለሞቹን ችላ ያለበትን ፣ ለኡለሞቹ ቋሚ ኢኮኖሚያዊ ገቢ የሚፈጥር ነገር ከመመስረ | እውቀት ብርሃን

ሱፊዩ ማህበረሰብ ኡለሞቹን ችላ ያለበትን ፣ ለኡለሞቹ ቋሚ ኢኮኖሚያዊ ገቢ የሚፈጥር ነገር ከመመስረት ይልቅ እድሜ ልካቸውን የነጋዴዎችን እጅ እንያዲያዩ ያደረገበትን አስነዋሪ ተግባር ቅጣቱን የሚያገኝበት ጊዜ ላይ ነን ።

ብዙ ኢማሞች የተሰውፍ ከባቸውን አውልቀው ሊጥሉ ስለሚችሉና በትንሹ ከወሃቢዮች ጋር አንድ ነን ሊሉ ስለሚችሉ ብዙ አትደናገጡ ።

ጉዳዩ ወንድ ልጅ አይጣ ነውና የትላንት ስህተታችን ዛሬም ነገም ዋጋ ያስከፍለናል ።

አሁንም ጊዜው አርረፈደም ሁላችንም በየሰፈሩ ያሉ አሊሞቻችን ወሃቢያን ከተጋፈጥኩ ከኢማምነት ልባረር እችላለው የሚል ስጋት ስለሚኖራቸው ከኋላቸው ደጀን እንደሆንን እናሳያቸው ፣ ድንገት ቢባረሩ እንኳ በምን መልኩ እነርሱን መኻደም እንደምንችል ካሁኑ እንወያይበትና መንገድ እንቀይስ