#ጥቆማ
ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና !
በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡
ይህን ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣ 7፣ 13፣ 14፣20፣ 21ቀጠሮ ፣28 ) ይካሄዳል።
በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።
#ማሳሰቢያ ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም ተብሏል።
#Share
መልዕክቱን አጋሩ
@ETV_57