Get Mystery Box with random crypto!

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ ተስፋ ያጣች ሴት | Fun ethiopia😂🤣

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ

ተስፋ ያጣች ሴት

ክፍል

...ሀና ልጇን ለማሶረድ መወሰን አቃታት ምክንያቱም ያረገዘችው ከምታፈቅረው ሰው ከኪሩቤል ነው ግን ኪሩቤል አድራሻውን በማጥፋቱ ልቶልደውም አልፈለገችም በዚ ተጨንቃ ሳለ አንድ እለተ እሁድ ሀና ፀጉር ቤቷን ከፍታ እያፀዳዳች ሳለ አንዲት ወጣትነት ያለፋት እርጅና ግን ገና ያልያዛት በ30ዎቹ መጨረሻ ላይ የምትገኝ ሴት ገርበብ ያለውን የፀጉር ቤት በር ገፋ አድርጋ ገባች ሀናም እንደወትሮዋ ሁሉ ምን ልታዘዝ ልትል ዞር ስትል ሁሌም ስትናፍቀው የኖረችውና ልታየው ግን ድፍረት ያጣችው ሰው ፊቷ ቆሟል በዛች ቅፅበት ለተመለከታት ስሜቷ ምን እንደነበር ለመግለፅ ቃል አይኖረውም ነበር... የሆነው ሆኖ ሀና ለጥቂት ሰከንድ ከተመለከተቻት ቡሃላ እማ ብላ በቁሟ ተዘረረች ይሄኔ የወንበሩ ጠርዝ ግንባሯን አግኝቷት ኖሮ በደም ተለወሰች... ሴትየዋ የሀና እናት አፀደ ነበረች በርግጥ የልጇን እዛ መኖር በጭራሽ አታውቅም ነበር እዛ ቤት በምን አጋጣሚ እንደገባችም እስካሁን ለእራሷ ለአፀደም እንቆቅልሽ ነው አንዳንዴ ሰዎች ሲጠይቋት... "እኔ የገባሁት ለምን እንደሆነ የፈጠረኝ አምላክ ነው የሚያውቀው ግን ግን" ...ትላለች አፀደ የኑሮ ፈተና ያጠወለገው ፊቷን በእጇ ደገፍ እያረገች "ግን ግን ልጄ በህይወት መኖሯን እንዳይ የቅዱስ ገብርኤል ፈቃድ ሆኖ ነው እያክለፈለፈ የወሰደኝ ብዬ አላመሰግነውም ምክንያቱም ልጄን በኔ ሰበብ ድንጋጤ ገሎብኝ ነበር..." ትልና አቀርቅራ ታነባለች... ሀና ሳትነቃ 3 ሳምንት ሆናት እናቷም የምታውቃቸውን ታቦቶች ሁሉ እየጠራች በፀሎት ካጠገቧ ሳትነቃነቅ ሰነበተች አንዳንዴ እዛው የሀና አልጋ አጠገብ ተንበርክካ... "አምላክ ሆይ ልጄን አሳይተኽ ስታበቃ አትንሳኝ እባክህ ከፈለክ ትንንሾቹን ውሰድ!!" ትላለች ይሄኔ ቴድሮስ ከሰማ ታድያ ጦርነት ይከፍታል... ሀና ነቃች ግን ነገሮችን ለማስታወስ ጊዜ ወስዶባት ቆይታ ስታስታውስና እናቷን በድጋሚ ከጎኗ ስታይ ትኩስ እንባዋ በተንጋለለችበት ጆሮዋ ውስጥ ሞላ ሀናም አንደበቷን መጠቀም ስላቃታት እናቷን ይቅርታ ለመጠየቅ አቅም አታ በአይኖቿ የእናቷን ልብ ለማኘኝት ተማፀነች እናቷ የሀናን መንቃት ስታይ እልልታዋ ሀኪም ቤቱን አወከው አምላኳን ለማመስገን ቃል አጣች ይሄን ያየ ሁሉ በአፀደና ልጇ ሁኔታ ስሜቱ ያልተነካ የለም እናትና ልጅ ከልብ ያስለቅሳሉ.... ቀናት አለፉ ሀና ከሀኪም ቤት ወታ እናቷ ቤት ናት እህትና ወንድሟ አድገዋል ሀና ዳግም የተወለደች እስኪመስላት ለመጀመርያ ግዜ በሚባል መልኩ ዛሬ የደስታ ጭላንጭል ይታይባታል እናቷ በመገኘቷ ደስተኛ ከመሆንዋ የተነሳ የት እንደነበረች ለመጠየቅ አልፈለገችም!... ቴድሮስና ሀና ሳይነጋገሩ 4 ወር አለፈ ሀናም ሀኪም ቤት በነበረችበት ጊዜና በመታመሟ ምክንያት ስለፅንሱ ምንም ሳትወስን የ6ወር ነብሰ ጡር ሆነች ግን ሀናን እንጂ የሀናን እናት የልጁ አባት አለመኖር አላሳሰባትም ሀናም ከቀን ወደቀን የኪሩቤል አለመመለስና የልጇ የወደፊት እጣ ያስጨንቃት ጀመር በዚም ምክንያት ሀና ብዙ ቀን ትታመማለች አንድ ቀን ማለዳ ሀና የሀኪም ቤት ቀጠሮ ኖሯት ሄደች... ይሄኔ ቤት የነበረው ቴድሮስ ብቻ ነበር... ይሄኔ በር ተንኳኳ ቴወድሮስም በር ከፈተ ኪሩቤል ነበር በርግጥ በአካል አያውቀውም እረስቶታል ኪሩቤል ግን ቴድሮስን አረሳውም... ሀናን እንደፈለጋትና የልጇ አባት እንደሆነ ሲነግረው ቴድሮስ ፊቱን አጨፍግጎ... "እስካሁን የት ነበርክ ?" ሲል ጠየቀ ኪሩቤልም ነገር ሳያንዛዛ "ሀገር ውስጥ አልነበርኩም!" አለ ቴድሮስ ግን "እዚ አትኖርም ዳግም እንዳትመጣ" ሲል አስጠነቀቀው.....

#ክፍል ይቀጥላል..... ለጓደኞቻችሁም አጋሮአቸው

ፍቅር እና ሳቅ
⚘➣ @etsubawi❥
══•ೋ•✧ ೋ✧•══
ሼር SHARE