Get Mystery Box with random crypto!

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ ተስፋ ያጣች ሴት | Fun ethiopia😂🤣

#በእውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_ለይ_የተመሰረተ

ተስፋ ያጣች ሴት

ክፍል

...ሀና ከኪሩቤል ጋር ማደሯ እጅግ በጣም ነበር ያስደነገጣት ፈፅሞ ይህ እንዲፈጠር አልፈለገችም ነበር በዚም ምክንያት ጧት ላይ ቀድሟት ነቅቶ ቁርስ እየሰራ ስታየው እራሷን አንቃ ብትገል ደስ ባላት ነበር ኪሩቤልን እንደገደለችው ተሰማት። አሁን አብረው አድረዋል ይህም ማለት ወደ ጀርመን የመመለስ እድል አይኖረውም ይህ ደግሞ በሷ ምክንያት መሆኑ ህሊናዋን እረፍት አሳጣት "ኪሩ እባክህ ይቅር በለኝ" አለች ከየት መጣ የማይባል እምባ ጉንጯን አልፎ በቅጡ ያልተሸፈኑ ጡቶቿን እያራሰ... "ያለፈው አልፏል ውዴ አትጨናነቂ ደግሞ ሰክረሽ እንደምታፈቅሪኝ ነግረሽኛል ስለዚ ካፈቀርሽኝ ለኔ በቂዬ ነው!" አለ በደስታ ፈገግ ብሎ ስስ ፀጉሮቿን እያሻሸ... ሀና እንባዋ እየባሰ መጣ ኪሩቤልን ከማጣቷ በላይ በሷ ምክንያት የሚጎዳው ጉዳት አሳሰባት... ኪሩቤል ደረቱ ላይ ልጥፍ አርጓት እረጅም ሰአት ቢቆይም ሀና ግን ልትናገረው የምትፈልገውን ነገር ለማውጣት ከራሷ ጋር ሙግት ገጥማ ነበር ይሄኔ "ሀኒ" አለ ኪሩቤል ፍርሃት ጭንቀትና እንባ በወረሱት አይኖቿ ተመለከተችው "እባክሽ በመሃላችን ስለነበረው መራራቅና ክፍተት እርሺ ከዛም ፍቅራችንን ብቻ እናዳምጥ ሀኒዬ አይናችንን ባይናችን እንይ አሁኑኑ አግቢኝ!! ከዛ ከፈለግሽ እዛ አወስድሻለው ካልፈለግሽ ደግሞ ሀገርሽ ላይ እንደንግስት እንከባከብሻለሁ..." አለ በአይኖቹ እየተማፀናት... ሀናም ይህን ስትሰማ ድሮ ቢሆን ምን ያህል በደስታ እንደምትሰክር አሰበች አሁን ግን ባዶ ተስፋ ሆነባት እናም ኪሩቤልን ከላይዋ ላይ ገፋ እያደረገች... "በቃህ ይሄ ሁላ ከንቱ ምኞት ነው ስለኔ ብዙ የማታውቀው ጉድ አለ... አንተጋ ለመምጣት ፕሮሰስ ጀምሬ ተስፋ በሰነኩበት ሰአት ቅዱስ የሚባል አውሬ በደካማ ጎኔ ገብቶ ህይወቴን አመሰቃቀለው ከዛም ወደ ሴተኛ አዳሪነቴ ተመለስኩ... ይህን ያረኩት ከሀገር ለመውጣት በቂ ገንዘብ ስላልነበረኝ ላጠራቅም ነበር ግን ፈጣሪ ያኔ ገና ቴዎድሮስ ልጅነቴን ሲነጥቀኝ እረስቶኝ ነበርና (H I V ) ኤች አይ ቪ በደምሽ ውስጥ አለ ተባልኩ እናም ያንቺ እጣ ሴተኛ አዳሪነት ነው ብለው ፈረዱብኝ... በቃ ወንዱን ሁሉ በተለይ ሀብታምና ባለስልጣን እየመረጥኩ ስበቀል ኖርኩ ግን በስተመጨረሻ ወላጅ አባቴ ፀጋዬ ገ/ማርያም አንሶላ ተጋፈፈኝ..." አለች ይህን ስትናገር በስሜት ጮክ ብላ ነበር ሀናን ለሚሰማት ልብ ወለድ ትረካ እንጂ እውነት የሷ ታሪክ አይመስልም ነበር... ኪሩቤል ይህን ሁሉ ጉድ ሲሰማ እራሱን አለመሳቱ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ ያሳያል... ሀና ንግግሯን ቀጠለች "እሺ አሁን ይሄን ሁሉ ጉዴን ሰምተሃል በላ ዝም አትበል እንደመጀመርያህ ያላንቺ አልኖርም... ምናምን በለኝ እ ዝም አትበለኝ ኪሩ አሁንስ አግብተኸኝ መኖር ትፈልጋለህ?" ኪሩቤል መቋቋም ተሳነው ምንም ሳይመልስላት ወጥቶ ሄደ... ኪሩቤል ከወጣ 2 ወር ሆነው ስለሱ ምንም ሰምታ አታውቅም ስልኩም ዝግ ነበር ሀና ስለኪሩቤል ብዙ ትጨነቃለች ስለሱ ምንም ባለመስማቷ ደግሞ ጭንትቷን እጥፍ አርጎባታል ይህ በንዲህ እንዳለ ሀና የወር አበባዋ ቀረ ለዚህም በመጠራጠር ሆስፒታል ስትሄድ የ2 ወር ነብሰ ጡር መሆኗን አረጋገጠች ከዚህ የባሰው ለሀና ያስደነገጣት ነገር ግን ከኤች አይ ቪ ነፃ ነሽ መባሏ ነበር... ይሄ ለሀና ተአምር ነበር... አላምን ብላ 3 ሀኪም ቤት ሄደች ግን ለውጥ የለውም ሀና ነፃ ናት... ግን አሁን እረፍዷል ኪሩቤል ጥሏት ሄዷል ይሄ ደግሞ ልጁን እንዳትወልደው ያደርጋታል ምክንያቱም ሀና ያለ አባት ልጅ ላታሳድግ ያለፈ ህይወቷ ያስገድዳታል.........

#ክፍል ይቀጥላል..... ለጓደኞቻችሁም አጋሮአቸው

ፍቅር እና ሳቅ
⚘➣ @etsubawi ❥
══•ೋ•✧ ೋ✧•══
ሼር SHARE