2022-05-10 10:49:01
#የነርቭ #ህመም #ዋና #ዋና #ምልክቶች
#መደንዘዝ: -ነርቮች መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመሪያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላክ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል። በጊዜው ተገቢ ህክምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። እጅ እና እግር ላይ ለሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት ሌሎች መንስኤዎች፡- እግር እና እጅ ላይ የተፈጠረ ከፍተኛ ጫና፣ ለብርድ መጋለጥ፣ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤ እና የቫይታሚን ቢ12 እና ማግኒዢየም እጥረት ናቸው።
#ህመም: - ሌላዉ የነርቭ ህመም ምልክት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው። የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል። ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በተጎዳው ቦታ ዙሪያ ብቻ ወይም ሰፊ የሰውነት ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል። ህመሙ ብዙ ጊዜ በምሽት ይባባሳል። ከነርቭ ጉዳት ውጪ የስኳር በሽታ፣ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ወይም የጀርባ አጥንት ሰረሰር ላይ የተፈጠረ ጉዳት ለከባድ የህመም ያጋልጠናል።
#የጡንቻ #ድካም: - ጡንቻ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት የሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእክት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን። በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል። በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። ጡንቻ መዳከም ከነርቭ ጉዳት ውጪ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ የዲስክ መንሸራተት፣ ስትሮክ የመሳሰሉ ህመሞች መንስኤ ይሆናሉ።
#የጡንቻ #መሸማቀቅ: - የእንቅስቅሴ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው። የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መካከለኛ ወይም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።
#የላብ #ችግር: - አውቶኖሚክ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል።
#ሽንት #ቤት #መመላለስ: - የሽንት ፊኛ ሽንትን በደንብ እንዲይዝ ብዙ ነርቮች አብረው መስራት አለባቸው። የነርቭ ጉዳት ሲፈጠር የሽንት ፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ይሞክራል። የነርቭ ጉዳት የሽንት ፊኛ ጡንቻዎች የሚያደርጉትን መኮማተር እና መላላት በተገቢው መልኩ እንዳያደርጉ ያስተጓጉላል። የሽንት ፊኛ ችግር ሌላ መንስኤ ሊኖረው ይችላል።
#ከባድ #ራስ #ምታት: - የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል አጭር ጊዜ የሚቆይ ከባድ ራስ ምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል።
#የሰውነት #ሚዛን #መጠበቅ #መቸገር: - የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው። ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብዎትም። የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።
#የነርቭ ችግር እንዳለ ከምልክቶች በተጨማሪ በምርመራ ከተረጋገጠ በቂ እረፍት በማድረግ፣ በመድሐኒቶች፣ በፊዚዮቴራፒ እንዲሁም እንደ ጉዳቱ መጠን በቀዶ ህክምና እንዲታከም ይደረጋል፡፡
868 viewsRaphael Raphael, 07:49