Get Mystery Box with random crypto!

Ethio pharmaceuticals and Health

የቴሌግራም ቻናል አርማ etpdhids — Ethio pharmaceuticals and Health E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etpdhids — Ethio pharmaceuticals and Health
የሰርጥ አድራሻ: @etpdhids
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 875
የሰርጥ መግለጫ

Info
A channel created for pharmaceutical product ,pharmacy service promotion , drug and health related information delivery .
For comment @demass_bot

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 09:36:01 የጡት ካንሰር ለምን ይከሰታል?

የጡት ካንሰር ሁልጊዜም የሚከሰተው በ genetic abnormality (በዘረ-መል ችግር) ምክያት ነው። የዘረመል ችግር በዘር የተላለፈ ወይም በዘር ያልተላለፈ ሊሆን ይችላል።

በዘር በሚተላለፍ የዘረ-መል ችግር ምክንያት የሚከሰት የጡት ካንሰር ከ5-10% ያህል ብቻ የሚሆነው ነው። ይህም ማለት ትክክለኛ ያልሆነ (የተቀየረ) ጂን ከወላጅ ሲወረስ የሚከሰት ነው።

የቀረው 90% ያህል የጡት ካንሰር ግን በዘር የማይተላለፍ ነው። ይህም ማለት ታማሚው ጤነኛ ዘረመል (gene) ከቤተሰብ ወርሶ/ሳ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ያ ጤነኛ gene ወደ ካንሰር አምጪነት ሲቀየር ነው

ይህም ማለት የጡት ካንሰር ካለባቸው 10 ሴቶች ውስጥ አንዷ ብቻ ናት በዘር የሚተላለፍ የጡት ካንሰር የሚኖርባት ሌሎቹ ዘጠኙ በቤተሰብ የጡት ካንሰር ታሪክ የሌለባቸው ነው የሚሆኑት።

ይህንን ማወቅ/ መረዳት በዘር ወይም በቤተሰብ የጡት ካንሰር ስለሌለብኝ እኔን አይዘኝም ብለን እንዳንዘናጋ ይረዳናል።

ለጡት ካንሰር ተጋላጭ የሚያደርጉ ነገሮች
- ማንኛውም ሰው ወንድም ሆነ ሴት በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አለው
- አንዳንዶች ከሌሎች ሰዎች በተለየ ከፍ ያለ ተጋላጭነት ሊኖራቸው ይችላል

በሃገራችን የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ባይኖሩም በሌላው አለም ግን ከስምንት ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር ትያዛለች

ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲወዳደር በጡት ካንሰር የመያዝ እድላቸው በጣም አነስተኛ ነው። ከ800 ወንዶች አንድ ወንድ ላይ ይከሰታል። ይህ ቁጥር ግን የሚናቅ አይደለም። ስለዚህም ወንዶች ከሴቶች እኩል ስለ ጡት ካንሰር በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል።

የጡት ካንሰር ተጋላጭነት የሚጨምሩ ነገሮች (risk factors)

1- እድሜ (ከ50 አመት በላይ መሆን)

2- የተቀየረ ጂን ከቤተሰብ መውረስ (BRCA1እና BRCA2 የሚባሉ ጂኖች)

3- የተራዘመ የወር አበባ ጊዜ: የመጀመርያ የወር አበባ ከ12 አመት በታች ማየት እና የወር አበባ የቆመበት ጊዜ ከ55 አመት በኋላ መሆን

3- የጡት የተፈጥሮ አይነት (በህክምና ቋንቋ dense breast የምንለው)

4- ከቤተሰብ አባላት ውስት የጡት ወይም የዘር ፍሬ ካንሰር (ovarian ca) ታሪክ መኖር

5- ለሌሎች በሽታዎች የሚሰጥ የጨረር ህክምና (radiation therapy)

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት እኛ በጥረታችን ልንቀይራቸው የማንችላቸው የጡት ካንሰር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ሲሆኑ ከታች የተዘረዘሩት ግን መቀየር የምንችላቸው ነገሮች ናቸው

1- የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

2- ከመጠን ያለፈ ውፍረት

3- ኢስትሮጅን እና ፕሮጄተሮን የተባሉ ሆርሞኖች የያዙ መድሃኒቶችን መውሰድ

4- የመጀመርያ ልጅን ከ30 አመት በኋላ መውለድ እና ጡት አለማጥባት

5- አልኮሆል መጠጦችን መጠጣት

6- ማጨስ

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ነገሮች ተጋላጭነትን ይጨምራሉ ማለት ነው እንጂ ቀጥታ ከጡት ካንሰር ጋር ይያያዛሉ ወይም የጡት ካንሰር ያመጣሉ ማለት አይደለም።

አንዲት ሴት ሁሉም ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁነታዎች (risk factors) ኖረዋት የጡት ካንሰር ላይዛት ይችላል። በተቃራኒው ደግሞ ምንም አይነት የሚታወቅ risk factors የሌላት ወጣት ሴት ደግሞ የጡት ካንሰር ሊይዛት ይችላል።

ስለዚህም ማስቀረት ወይም መቀነስ የምንላቸውን ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ማስተካከል, በየጊዜው ጡታችንን መፈተሽና ከሃኪም ጋር በመመካከር ምርመራዎችን ማድረግ ብቸኛው መፍትሄ ነው።
141 viewsRaphael Raphael, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:20:15 "ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?"

በስራ ገበታ ሳለን ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ "የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው" ብለው ሳያበቁ ቱከት ተቅማጥ ታመው ማየት የተለመደ ነገር ነው ።

ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?

ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ ፣ የሳምባ ምች ፣ የጀሮ ምርቀዛ ('ኢንፌክሽን') እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡

ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?

- የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡

በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ እንዲሁም በከተማዎች አልፎ አለፎ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ ፣ ቅቤ ፣ ሻይ ፣ ዉሃ በስኳር የመሳሰሉትን መስጠት ለኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡

- ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡

እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8-12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡

በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር ይቻላል፡፡

- ከስድስት ወር ቀደመው ሌላ ነገር ቢጀምሩ ምን የጤና ችግር ይገጥማቸዋል?
ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል::
ልጆች ለተቅማጥ በሽታ እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል::

- ተጨማሪ ምግብ ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ እሳ?
ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
ልጆች ለመቀጨጭና ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡

ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?

- ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት
የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡

- የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች
o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል
o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል
o የህጻናት ሆድ ድርቀት
o የወተት አለርጂ
o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡
o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል

አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት
መልካሙን ሁሉ ተመኘው
ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም
Via hakim
311 viewsRaphael Raphael, 15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 11:26:42 አጥንት ወስጥ ተቀብረው የቀሩ ጥርሶች Impacted teeth

የተቀበረ ጥርስ በሆነ ምክንያት ድድን ከፍቶ ለመውጣት ያልቻለ ጥርስ ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ጥርስ በከፊል ብቻ ድድን ከፍቶ ወደ ኣፍ ብቅ ሊል ይችላል ፣ ከፊል መቀበር (partial or secondary impaction) የሚባል ዓይነት።

ብዙውን ጊዜ ፣ ​​የተቀበሩ ጥርሶች ምንም ግልጽ ምልክቶች አያሳዩም እና ብዙውን ጊዜ ሀኪምዎ በኤክስሬይ ሊያገኛቸው ነው የሚችለው።

የተቀበሩ ጥርሶች ምልክቶች

በአንዳንድ ሁኔታዎች የተቀበረ ጥርስ የሚከተሉትን ጉዳቶች ሊያስከትል ይችላል-
ቀይ ፣ ያበጠ ወይም የድድ መድማት የተቀበረው ጥርስ ዙሪያው ላይ
መጥፎ የአፍ ጠረን
መጥፎ ጣዕም በአፍዎ ውስጥ
አፍዎን ለመክፈት ችግር
አፍዎን ሲከፍቱ ፣ ወይም ሲያኝኩ እና ሲነክሱ ህመም

ምልክቶቹ ከሳምንታት ወይም ከወራት በላይ ሊመጡ እና ሊሄዱ ይችላሉ።

የተቀበረ ጥርስ ምን ያስከትላል?
በአጠቃላይ ፣ አፍዎ ለእሱ በቂ ቦታ በማይኖርበት ጊዜ ጥርስ ተቀብሮ ሊቀር ይችላል። ይህ የጄኔቲክስ ወይም የአጥንት አለማደግ ውጤት ሊሆን ይችላል።

የትኞቹ ጥርሶች ብዙውን ጊዜ ይቀበራሉ?

ብዙውን ጊዜ የሚያድጉ የመጨረሻ ጥርሶች የሆኑት (wisdom tooths) ጥርሶች - በተለምዶ ከ 17 እስከ 21 ዓመት ባለው ዕድሜ ክልል ሊበቅሉ ይችላሉ። የመጨረሻ ጥርሶች ወይም wisdom tooths በመባልም ይታወቃሉ - በሚያድጉበት ጊዜ መንጋጋ ብዙውን ጊዜ ማደግ ያቆማል።

ስለዚህ አፍ እና መንጋጋ እነሱን ለማስተናገድ በጣም ትንሽ ሊሆኑ ይችላሉ። በቂ የአጥንት ዕድገት ከሌላቸውና ለጎላ ችግር ካስከተሉ በተለምዶ በቀላል ቀዶ ህክምና ይወገዳሉ። ትንሽ መንጋጋ ካለዎት በመጨረሻ ወይም wisom tooths ጥርሶች ላይ ተጽዕኖ የማድረግ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

ከታችኛው የመጨረሻ መንጋጋ በመቀጠል የላይኛው የመጨረሻ ወይም ዊዝደም ጥርስ በመቀጠልም የላይኛው መንጋጋ የውሻ ክራንቻ ጥርሶች ናቸው።

እነዚህ ጥርሶች በአፍዎ ውስጥ የበለጠ አስፈላጊ ሚና ስለሚጫወቱ ፣ እነዚህ ጥርሶች ከማስወገድ ይልቅ ከተቀበሩበት አጥንት ወደ አፍ እንዲወጡ የሚያበረታቱ ሕክምናዎችን መሞከሩ ይበልጥ ተመራጭ ነው።

የተቀበሩ ጥርሶች እንዴት ይታከማሉ?

የተቀበረ ጥርስ እንዳለዎት ከተጠራጠሩ በተቻለ ፍጥነት የጥርስ ሀኪምዎን ይመልከቱ። የተቀበረ ጥርስ የህመም ምልክት እያመጣ መሆኑን ለማወቅ ሀኪምዎ ጥርሶችዎን መመርመር እና የጥርስዎን ኤክስሬይ ሊወስዱ ይችላሉ። ጥርሱ የተቀበረ ከሆነ የሕክምና ጥቅሞችን እና አደጋዎችን መወያየት ይችላሉ።

የሕክምና አማራጮች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ:

በቦታው መጠበቅ እና መከታተል: የተቀበረ ጥርስዎ ምንም ምልክቶች የማያመጣ ከሆነ ፣ የጥርስ ሐኪምዎ የመጠበቅ እና የማየት አማራጭ ሊጠቁም ይችላል። በዚህ መንገድ ጥርሱን በቀዶ ጥገና ከማስወገድ ይልቅ ፣ ማንኛውም ችግር ሲከሰት ለማየት እንዲችሉ የጥርስ ሀኪሙ በየጊዜው ይከታተለዋል::

ቀዶ ጥገና:

የተቀበረ ጥርስ ህመም እና ሌሎች ደስ የማይሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ካጋጠመዎት ፣ የጥርስ ሀኪምዎ በተለይ የተቀበሩ የመጨረሻ የመንጋጋ ጥርሶች ላይ የማውጣት ቀዶ ጥገናን ሊመክር ይችላል። የተቀበረው ጥርስ በሌሎች ጥርሶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ካሳደረ እንዲወጣ ይመክራሉ።

የጥርስ ማስወገጃ ቀዶ ጥገና ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በቀላል የቀዶ ጥገና ሐኪም ቢሮ ውስጥ እንደ የተመላላሽ ሕክምና ሂደት ነው ፣ ይህ ማለት እርስዎ በታከሙበት ቀን ወደ ቤት መሄድ ይችላሉ። የቀዶ ጥገና ሂደቱ ብዙውን ጊዜ ከ 45 እስከ 60 ደቂቃዎች ይወስዳል ፣ እና ቀዶ ጥገናው የሚከናወነው ቦታዋ ላይ ማደንዘዣ (Local anesthesia) በመስጠት ይሆናል።

ማገገም ከ7 እስከ 10 ቀናት ሊወስድ ይችላል ፣ ነገር ግን ቀለል ያለ ቀዶ ጥገና ስለሆና በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ወይም ትምህርት ቤት መመለስ መቻል አለብዎት።

Via hakim
284 viewsRaphael Raphael, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 14:02:57 በተለምዶ "ጆሮ ደግፍ" (Mumps) ስለሚባለው በሽታ እንወያይ

1.ጆሮ ደግፍ (mumps) ምንድን ነው

-ጆሮ ደግፍ (mumps)የምንለው በሽታ በብዛት የሚያጠቃው በጆሯችን ስር የሚገኙትን ምራቅን የሚያመርቱትን የምራቅ አመነጪ ከረጢቶች (salivary glands) ሲሆን ይህም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች ላይ mumps በሚባል ቫይረስ በበሽታው ከተጠቃ ሰው በሚስልበት እና በሚያስነጥስበት ጊዜ ከላይኛው የመተነፈሻ አካል በሚወጣ ጠብታዎች ወደ ጤነኛ ሰው መተንፈሻ አካል በሚገባበት ጊዜ እነዲሁም በንክኪ ይተላለፋል።

-እንደ የአለም የጤና ድርጅት (WHO) አገላለፅ በአብዛኛው ይህ በሽታ በብዛት በአማካይ ከ5-9 አመት የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ልጆች ላይ ይከሰታል።ይህ በሽታ በተለይም የmumps ክትባትን ያልወሰዱ ሰዎች ላይ ይስተዋላል።

አጋላጭ ምክንያቶቹስ?

-የmumps ክትባት ያልወሰዱ፣ደካማ የበሽታ መከላከያ አቅም (immune defficiency) ያላቸው ሰዎች ተጋላጭ ናቸው።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

-ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ ከገባ በዃላ የበሽታውን ምልክት ምልክት እስከሚያሳይ ከ2-3 ሳምንት ጊዜ ሊቆይ ይችላል።

-ከጆሮ ዝቅ ብሎ ባለው የፊት ክፍል እብጠት መኖር ፣ ትኩሳት ፣ በምራቅ ከረጢት አካባቢ የህመም ስሜት፣በሚያኝኩበት እና በሚውጡበት ጊዜ የህመም ስሜት መኖር ፣የእራስ ምታት ፣ የጡንቻ ህመም ፣ ትኩሳት፣ የድካም ስሜት፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ይስተዋላል።

የሚያመጣውስ መዘዝ?

-Mumps በሽታ በሰውነታችን አካሎች ላይ የመቆጣት እና የማበጥ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ለምሳሌ የወንድ የዘር ፍሬ መቆጣት (orchitis)፣ የሴት ዘር ማኮረቻ መቆጣት (Oophoritis)፣ በተለምዶ የማጅራት ገትር (meningitis)፣ የቆሽት መቆጣት (pancreatitis)፣ የመገጣጠሚያ መቆጣት (arthritis)፣ ለመስማት መሳን (deafness) ሊከሰት ይችላል።

እንዴት መከላከል እንችላለን?

-ወላጆች ልጅዎን የmumps ክትባት (MMR vaccine) መውሰድ በተለይ እድሜያቸው ከ 12-15 ወር ህፃናት የመጀመሪያውን ዙር ከዛም ሁለተኛውን ዙር ክትባት ደግሞ እድሚያቸው ከ4-6 አመት ክልል ሲሆኑ መውሰድ ከበሽታው ተጋላጭ እነዳይሆኑ ይረዳል።

ህክምናዎቹስ ምንድን ናቸው?

-ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ ስለሆነ በበሽታው የተጠቃውን ሰው ቢያንስ ለይቶ ማቆየት፣ ፈሳሽ ነገሮችን በብዛት መውሰድ፣ አሲዳማ ምግቦችን ለምሳሌ እንደ ብርቱካን እና ሎሚ አለመጠቀም፣ ብዙ ማኘክ የሚፈልጉ ምግቦችን አለመመገብ፣ ህመም ካለ የህመም ማስታገሻ በሀኪም ትእዛዝ መውሰድ፣ ሞቅ ባለ ወይም ቀዝቀዝ በላ ነጠር እብጠቱ ላይ መያዝ እንዲሁም በቂ እረፍት ማድረግ የህክምናው አካል ነው።

-በቫይረሱ ምክንያት ተያያዥ መዘዞች ካሉ እንደ አስፈላጊነቱ ተኝቶ መታከም ሊጠበቅ ይችላል።

-በሽታው በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ስለሆነ ፀረ ባክቴሪያ መጠቀም ምንም ጠቀሜታ የለውም።
299 viewsRaphael Raphael, 11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 17:59:52 በእግር ጅማት ላይ ያለ የደም መርጋት (DVT)

ጥልቅ ደም መላሽ ቧንቧዎች (Deep Venous Thrombosis) በሰውነትዎ ውስጥ ባሉ አንድ ወይም ብዙ ጥልቅ ደም መላሾች ውስጥ የደም መርጋት ሲፈጠር ይከሰታል።

DVT የእግር ህመም ወይም እብጠት ሊያስከትል ይችላል ነገር ግን ምንም ምልክት ሳይታይበት ሊከሰት ይችላል።

ጥልቅ ደም መላሽ ቧንቧዎች በጣም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱም በደም ስርዎ ውስጥ ያለው የደም መርጋት ሊሰበር፣ በደምዎ ውስጥ ሊያልፍ እና በሳንባዎ ውስጥ ሊጣበቅ ስለሚችል የደም ፍሰትን ይዘጋል።

ሆኖም የደም ፍሰት ምንም የDVT ምልክት ሳይኖር ሊከሰት ይችላል።

ምልክቶች

በተጎዳው እግር ላይ እብጠት
በእግርዎ ላይ ህመም
ቀይ ወይም ቀይ ቀለም ያለው ቆዳ
በተጎዳው እግር ላይ የሙቀት ስሜት

የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

ዕድሜ ከ60 በላይ መሆንዎ
ለረጅም ጊዜ መቀመጥ
ረጅም የአልጋ እረፍት ለምሳሌ በሆስፒታል
ጉዳት ወይም ቀዶ ጥገና
እርግዝና
በዘር የሚተላለፍ የደም መርጋት ችግር
ከመጠን በላይ መወፈር
ማጨስ
የልብ ድካም
የካንሰር ህክምና ዓይነቶች የደም መርጋት አደጋን ይጨምራሉ።

መቼ ወደ ሐኪም እንሂድ

የደም መርጋት ምልክቶች ከታዩ ሐኪምዎን ያነጋግሩ
የደም ፍሰት ምልክቶች ከታዩ የአደጋ ጊዜ የሕክምና እርዳታ ይፈልጉ
የደም ፍሰት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፣
ድንገተኛ የትንፋሽ ማጠር
የደረት ህመም
ምቾት ማጣት
ፈጣን የልብ ምት
ፈጣን መተንፈስ

ምንጭ: cleverlandclinic
445 viewsRaphael Raphael, 14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 07:34:31
466 viewsRaphael Raphael, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:49:08

570 viewsRaphael Raphael, 18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 23:22:20
679 viewsDemiss Mohammed, 20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 07:19:00
791 viewsRaphael Raphael, 04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 18:27:04 የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkeypox) ምንድን ነው?

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Monkey Pox Virus) በሚባል ቫይረስ የሚከሰት እና አልፎ አልፎ የሚታይ በሽታ ነው። በሽታው ሲከሰት እንደ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት ማለት ምልክቶች የሚታዩ ሲሆን ሰውነት ላይ የሽፍታ አይነት ነጠብጣቦች ይታያሉ። ለበሽታው ይህ ነው የሚባል የተረጋገጠ ህክምና ባይገኝለትም ብዙውን ጊዜ በራሱ የመዳን ባህሪ አለው።

ይህ በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው እ.አ.አ በ1958 ዓ.ም. ሁለት ለጥናት ያገለግሉ የነበሩ ዝንጀሮዎች በበሽታው ተጠቅተው በተገኙ ጊዜ ነበር። ስሙ ከዝንጀሮዎች ጋር ተያይዞ ይሰየም እንጂ በሽታው ከዝንጀሮ ይመጣል ማለት ግን አይደለም።

ሳይንቲስቶች ስለመነሻው እርግጠኞች ባይሆኑም የበሽታው መነሻ በአፍሪካ የሚገኙ አይጦች እና ሽኮኮዎች ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ከዚህም በመነሳት በሽታውን በሁለት ቤተሰብ ከፍለውታል።

የመካከለኛው አፍሪካ እና የምዕራብ አፍሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሚል። እንደ ባለሞያዎቹ ትንታኔ የመካከለኛው አፍሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከምዕራብ አፍሪካው ይልቅ ለከፍተኛ ህመም የመዳረጉ እና አልፎ ተርፎም ለሞት የማብቃት እድሉ ከፍ ያለ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ እና መደበኛው ፈንጣጣ የሚከሰቱት ተመሳሳይ ባህሪ ባላቸው ቫይረስ ነው። ስለዚህ የፈንጣጣ ክትባት የወሰደ ሰው በቀላሉ እራሱን ከዝንጀሮ ፈንጣጣም መከላከል ይችላል። ሆኖም ፈንጣጣ ስጋት መሆኑ ካቆመ ዘመናት ስለተቆጠሩ እና ክትባቱም አለመሰጠቱ ሰዎች በዚህ በሽታ በቀላሉ እንዲጠቁ እያደረጋቸው ይገኛል።

ከዚህ ቀደም ይህ በሽታ በተደጋጋሚ የተከሰተው በአፍሪካዊቷ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ነው። አልፎ አልፎም በተለያዩ ሀገራት የተከሰተ ሲሆን በ2003 እና በ2021 ዓ.ም. በአሜሪካ ተከስቶ ነበር።
ምልክቶቹ ምንድናቸው?

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምልክቶች ከፈንጣጣ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ቢሆኑም ከመደበኛው ፈንጣጣ ምልክቶች አንጻር ግን ቀለል ያሉ ናቸው። በሽታው ሲከሰት የሚከተሉትን አይነት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ:-

ትኩሳት (fever)
ብርድ ብርድ ማለት (chills)
ራስ-ምታት (headache)
ድካም (fatigue)
የጡንቻ ህመም

እነኚህን ምልክቶች ተከትሎ ሽፍታ የመሰሉ እብጠቶች በሰውነት ላይ ከተከሰቱ በሽታው የዝንጀሮ ፈንጣጣ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ሲጀምር ሽፍታው ቀላ ያለ ሆኖ ነው የሚጀምረው ከዛም ቀስ በቀስ መጠኑ ከፍ እያለ እና መግል እያዘለ ይሄዳል።

እንዴት ይተላለፋል?

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በበሽታው ከተጠቃ እንሰሳ ወይም ሰው ጋር በሚደረግ አካላዊ ንክኪ ይተላለፋል። መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም በበሽታው የተጠቃ ሰው በሚያስነጥስበት እና በሚያስልበት ጊዜ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ሊያስተላልፍ ይችላል። ይህ ግን እንደ ሌሎች በትንፋሽ የሚተላለፉ ቫይረሶች (communicable diseases) በቀላሉ የሚከሰት አይደለም።

ሌላው መተላለፊያ መንገድ በበሽታው የተጠቃ ሰው የነካቸውን ቁሶች ሌሎች ሰዎች ሲነኩ ቫይረሱ የመተላለፍ እድል ይኖረዋል።

መከላከያ መንገዶች

በበሽታው ከተጠቁ እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ
በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች ጋር ቁሶችን አለመጋራት
እጃችንን በሳሙና በአግባቡ ማጽዳት
በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች ጋር አካላዊ ንክኪ አለማድረግ ወይም በበሽታው የተጠቃ ሰውን ስንረዳ የተለያዩ የጥንቃቄ መሳሪያዎችን መጠቀም አለመዘንጋት። ማስክ፣መነጽር፣ጓንት ወዘተ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ገዳይ ነውን?

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ከመደበኛው ፈንጣጣ አንጻር ቀላል በሽታ ነው። ይሁንና ለሞት የማብቃት እድልም አለው። በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች 10% (እንደ WHO ከ3-6%) የሚሆኑት ለሞት እንደሚዳረጉ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ምንጭ: EthioTenna
911 viewsDemiss Mohammed, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ