Get Mystery Box with random crypto!

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . . ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ | የሰላም መልዕክተኞች በኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . .

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ ሕይወት አለ! ሌላ አቅጣጫ አለ! ሌላ አማራጭ አለ!

• እውነት ነው፣ ተምሬ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር . . . የመማሩን እድል ካላገኘሁ ግን ሕይወትን ውብ የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
• እውነት ነው፣ ፍቅረኛ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ትክክለኛ ፍቅረኛ ካላገኘሁ ግን ትክክለኛ ሕይወት የምመራበት ብዙ እድሎች አሉኝ፡፡
• እውነት ነው፣ ትዳሬ በሰላም ቀጥሎ ቢሆንና ባይፈርስ ጥሩ ነበር . . . አንዴ ከሆነና ሁኔታውን በፍጹም ማደስ ካልቻልኩ ግን የተዝረከረከውን ሕይወቴን አፋፍሼ፣ ሰብስቤና እንደገና አደራጅቼ በአዲስ መልኩ ሕይወት ይቀጥላል፡፡
• እውነት ነው፣ የምወደው ስራ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ሁኔታው ያንን ለማግኘት ካልፈቀደልኝ ግን ባለኝና ካለሁበት በመነሳት የማድግበትን መንገድ የመፈለግ መነሳሳቱ አለኝ፡፡

በአጭሩ፣ ሕይወት እኔ እንደምፈልጋት ብትሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ለምን አልሆነም ብዬ ደብቶኝ አልውልም፡፡ ቀና እላለሁ! ብርቱ ሰው ለመሆን እወስናለሁ! ስብር አልልም! አልደካክምም!

መንጭ : ዶ/ር እዮብ ማሞ


#ሰላም_ለሁሉም #teshe